መልዕክት ለወጣቶች

131/511

ትክክለኛ የሆነ ክርስቲያናዊ ልምምድ

በወጣቶች መካከል መሰረታዊ የሆነ አጠቃላይ ለውጥ ከሌለ በስተቀር በሰማይ ጉዳይ ተስፋ እንደሚቆርጡ አየሁ፡፡ እንዳይ ከተደረኩት በመነሳት እውነትና ኃይማኖት አለን ከሚሉት መካከል በትክክል የተለወጡት ከግማሽ የማይበልጡ ናቸው፡፡ የተለወጡ ቢሆኑ ኖሮ ለእግዚአብሔር ክብር ፍሬ ያፈሩ ነበር፡፡ ብዙዎቹ እውነተኛ መሰረት በሌለው በግምታዊ ተስፋ እየተደገፉ ናቸው፡፡ ምንጩ ንፁህ ስላልሆነ ከምንጩ የሚፈሱ ጅረቶችም ያልነፁ ናቸው፡፡ ምንጩን ካነፃችሁ ጅረቶቹም ይነፃሉ፡፡ MYPAmh 88.1

ልባችሁ ትክክለኛ ከሆነ ቃላቶቻችሁ፣ አለባበሳችሁ፣ ድርጊታችሁም ትክክል ይሆናል፡፡ እውነተኛ እግዚአብሔርን መምሰል በሰዎች ውስጥ ጠፍቷል፡፡ ግድ የለሽ፣ አሿፊና የፀሎት ሕይወት የሌለውን ሰው ክርስቲያን ነው ብለን ከመቀበል የበለጠ የጌታን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ሌላ ነገር የለም፡፡ ክርስቲያን ሥጋዊ ፍላጎቶቹን ድል አድርጓል፡፡ በኃጢአት ለታመመችው ነፍስ ፈውስ አለ፡፡ ፈውሱም ኢየሱስ ነው፡፡ ክቡር አዳኝ ! ፀጋው ለደካማውም በቂ ነው፡፡ ብርቱውም ቢሆን የእርሱ ፀጋ ከሌለው በስተቀር ይጠፋል፡፡ MYPAmh 88.2