መልዕክት ለወጣቶች

130/511

ምን ይጠቅመዋል?

ክርስቶስ እያንዳንዱን ግለሰብ እንዲያስብ ይጠራዋል፡፡ እውነተኛ ስሌት አስላ፡፡ በአንዱ ሚዛን ላይ ኢየሱስን ማለትም ዘላለማዊ ሐብትን፣ ሕይወትን፣ እውነትን፣ ሰማይንና ኢየሱስ በዳኑት ነፍሳት የሚደሰተውን ደስታ አስቀምጡ፡፡ በሌላኛው ሚዛን ላይ ደግሞ ዓለም ሊሰጥ የሚችለውን እያንዳንዱን ስሜትን የሚስብ ነገር አስቀምጡ፡፡ በአንደኛው ሚዛን ላይ የራስህን ነፍስና አንተ ለመዳናቸው ምክንያት ልትሆን የምትችላቸውን ነፍሳት መጥፋት አስቀምጥ፡፡ በሌላኛው ሚዛን ላይ ለራስህም ሆነ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ሕይወት ጋር የሚስተካከል ሕይወትን አስቀምጥ፡፡ ለአሁንና ለዘላለም መዝን፡፡ በእንዲህ ዓይነት ስራ ተሰማርተህ እያለህ ክርስቶስ እንዲህ ይላል ፡- «ለሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍና ነፍሱን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?» MYPAmh 86.7

እግዚአብሔር በምድራዊ ነገሮች ፋንታ ሰማያዊውን ነገሮች እንድንመርጥ ይፈልጋል፡፡ በፊታችን ዘላለማዊ ሀብትን የማካበት አጋጣሚዎችን ክፍት አድርጎልናል፡፡ ከፍ ላሉ ዓላማዎቻችን ማበረታቻና ምርጥ ለሆኑ ሀብቶቻችን ደህንነትን ይሰጠናል፡፡ እንዲህ ይላል፡- «ሰውን ከንፁህ ወርቅ የበለጠ ውድ አደርገዋለሁ፤ እንዲያውም ሰውን ከኦፍር ወርቅ የበለጠ የከበረ አደርገዋለሁ፡፡” ብል የሚበላውና ዝገት የሚያበላሸው ሀብት በሚጠፋበት ጊዜ የክርስቶስ ተከታዮች በሰማያዊው በማይጠፋ ሀብት ይደሰታሉ፡፡ Christ’s Object Lessons P. 374. MYPAmh 87.1