መልዕክት ለወጣቶች

128/511

ሰፊው መንገድ

በሰፊው መንገድ ላይ ያሉ በሙሉ በውጫዊ ማንነታቸው፣ በአለባበሳቸውና በመንገዱ ላይ ባሉ ደስታዎች ተጠምደዋል። ስለ ጉዞአቸው ፍፃሜና በመንገዱ መጨረሻ ላይ ስለሚጠብቃቸው ጥፋት ባለማሰብ በዚህ መንገድ ባለው ደስታና ፈንጠዚያ በሙሉ ነፃነት ይደሰቱበታል። በየቀኑ ወደ ጥፋታቸው እየቀረቡ ናቸው፤ ሆኖም በእብደት ወደዚህ ጥፋት እየፈጠኑ ይጣደፋሉ። ኦ! MYPAmh 85.2

ይህንን ሳይ ምንኛ አሰቃቂ ነበር! በዚህ ሰፊ መንገድ ላይ “ለዓለም ሙተናል፤ የሁሉም ነገር ፍፃሜ ቀርቧል፤ ተዘጋጁ::” የሚል ፅሁፍ ያለባቸው ብዙዎች ሲሄዱበት አየሁ። በፊታቸው ላይ ከተገነዘብኩት የሃዘን ጥላ በስተቀር በሌላው ሁሉ በዙሪያቸው ያሉትን ከንቱዎች ይመስሉ ነበር። ንግግራቸውም ልክ በዙሪያቸው እንደነበሩ ግድ የለሾችና ሐሳብ የለሾች ነበር። ነገር ግን አልፎ አልፎ በታላቅ እርካታ በልብሳቸው ላይ ተጽፈው ወደ ነበሩ ቃላት ሌሎችም ተመሳሳይ ቃላት በልብሳቸው ላይ እንዲኖራቸው በመጠየቅ ያመለክቱ ነበር። በሰፊው መንገድ እየሄዱ ሳለ ራሳቸውን ግን በጠባቡ መንገድ ላይ ከሚሄዱት ጋር እንደሆኑ ይናገራሉ። በዙሪያቸው ያሉት ግን “በእናንተና በእኛ መካከል ምንም ልዩነት የለም፤ሁላችንም ተመሳሳይ ነን፤ አለባበሳችንም፣ ንግግራችንም አንድ ነው” MYPAmh 85.3

ይላሉ። አንዳንድ ሰንበት ጠባቂዎች ነን ባዮች ከዓለም ጋር መስማማታቸውን እንዳይ ተደረግሁ። ኦ! ይህ ድርጊታቸው ለሚያምኑት እምነታቸውም ሆነ ለእግዚአብሔር ሥራ ውርደት እንደሆነ አየሁ። ለእምነታቸው ውሸትን ይሰጣሉ። ከዓለም ልዩ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ ነገር ግን በአለባበሳቸው፣ በንግግራቸውና በድርጊታቸው እነርሱን ለመምሰል እጅግ የቀረቡ ከመሆናቸው የተነሣ ምንም ልዩነት የላቸውም:: በማንኛውም ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት ሊነካና በሐዘን አልጋ ላይ ሊጋደም የሚችለውን ሟች ሥጋቸውን ሲያስውቡት አየሁ። ከዚያም ወደ መጨረሻው መለወጣቸው ሲቃረቡ አካላቸውን የሞት ሰቆቃ ያሰቃያቸውና «ለመሞት ተዘጋጅቻለሁን? በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት ለመቅረብና ታላቁን ምርመራ ለማለፍ ተዘጋጅቻለሁን?” MYPAmh 85.4

የሚለው ታላቁ ጥያቄ ይሆናል። ከዚያም አካላቸውን ስለ ማሸብረቅ ምን እንደሚሰማቸው ጠይቋቸው። በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ መዘጋጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚሰማቸው ከሆነ ወደ ኋላ ተመልሰው ባለፈው ጊዜ መኖር የሚችሉ ቢሆኑ ኖሮ ሕይወታቸውን እንደሚለውጡ፣ ከዓለም ሞኝነት፣ ከንቱነትና ኩራት እንደሚርቁና አካላቸውን በጨዋ አለባበስ በማስዋብ በዙሪያቸው ላሉት መልካም ምሳሌ እንደሚያሳዩ ይነግሩአችሁ ነበር። ለእግዚአብሔር ክብር ይኖሩ ነበር። ራስን መካድና ትሁት ሕይወትን መኖር ለምንድን ነው እንደዚህ የሚከብደው? MYPAmh 85.5

ለዚህ ምክንያቱ ክርስቲያን ነን ባዮች ለዓለም ስላልሞቱ ነው። ከሞትን በኋላ መኖር ቀላል ነው። ነገር ግን ብዙዎች የግብፅን ዱባና ሽንኩርት ይናፍቃሉ። ልክ እንደ ዓለማውያን ለመልበስና የእነርሱን መሰል ድርጊት ለመፈፀም ዝንባሌ እያላቸው ግን ወደ ሰማይ መሄድ ይፈልጋሉ። እንዲህ ዓይነቶቹ በሌላ መንገድ ላይ እየወጡ ያሉ ናቸው። እነዚህ በቀጭኗና በጠበበችው ደጅ አይገቡም:: MYPAmh 85.6

እንዲህ ዓይነቶች ምክንያት የላቸውም። በሌሎች ላይ ተፅእኖ ለማሳደር በማለት ብዙዎች እንደ ዓለም ይለብሰሉ። ነገር ግን በዚህ ነጥብ ላይ አሳዛኝና አደገኛ ስህተት ይፈፅማሉ። እውነተኛና የሚያድን ተፅእኖ እንዲኖራቸው ከፈለጉ በእምነታቸው እየኖሩበትና በተቀደሰ ተግባር እያሳዩ በክርስቲያንና በዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ያጉሉት። አለባበስ፣ ቃላትና ተግባሮች ለእግዚአብሔር መናገር እንዳለባቸው አየሁ። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ተጽእኖ በሁሉም ላይ ያርፍና ሁሉም ሰዎች እነዚህ ከኢየሱስ ጋር አብረው እንደነበሩ ያውቃሉ፡፡ የማያምኑ ሰዎች እኛ የምናምነው እውነት ቅዱስ ተፅእኖ እንዳለው ያያሉ። ያ በክርስቶስ ምፃት ያለው እምነትም የወንድንም ሆነ የሴትን ባህሪይ ይነካል። ማናቸውም ቢሆኑ የእነርሱ ተፅእኖ ለእውነት እንዲመሰክር የሚመኙ ከሆነ ያንን ሕይወት ይኑሩበት፤ የዋህ የሆነውን ምሳሌም ይከተሉ። MYPAmh 86.1