መልዕክት ለወጣቶች
ከዓለም ጋር መስማማት
በጠባቡ መንገድ ላይ የሚጓዙ በጉዞው መጨረሻ ላይ ስለሚኖራቸው ደስታና ፍስሐ ይናገራሉ። ፊታቸው ብዙውን ጊዜ ያዘነ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ በተቀደሰ ደስታ ያበራል። በሰፊው መንገድ እንደሚሄዱ ቡድኖች አይለብሱም፤ አይናገሩም፤ አያደርጉም። ሊከተሉት የሚገባ ምሳሌ ተሰጥቷቸዋል። የሐዘን ሰው የነበረውና ሐዘንንም የተለማመደው ኢየሱስ ራሱ ሄዶበት መንገዱን ከፍቶላቸዋል። ተከታዮቹ ዱካውን ይከተሉና ደስታና መፅናናትን ያገኛሉ። ዱካውን የሚከተሉ ከሆነ እርሱ መንገዱን ያለ ውድቀት እንደዘለቀ አነርሱም ይዘልቃሉ። MYPAmh 85.1