መልዕክት ለወጣቶች
ሐሳብን መቆጣጠር
ሰይጣን ከተጠናወተው ሁኔታ ራሳችሁን አርቁ፤ አእምሮአችሁ ለእግዚአብሔር ከላችሁ ታማኝነት እንዲዋዥቁ አትፍቀዱ፡፡ በክርስቶስ አማካኝነት ደስተኛ መሆን ትችላላችሁ፤ መሆንም አለባችሁ፡፡ ራስን የመቆጣጠር ልምዶችንም መለማመድ አለባችሁ፡፡ አስተሳሰባችሁ ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገዛት አለበት፡፡ ስሜቶቻችሁም ለግንዛቤና ለኃይማኖት መገዛት አለባቸው፡፡ አስተሳሰባችሁ ምንም ገደብ ወይም ቁጥጥር ሳይደረግበት አመጽ ለማካሄድና የራሱን መንገድ እንዲከተል የተሰጣችሁ አይደለም:: አስተሳሰቦቻችሁ ስህተት ከሆኑ ስሜቶቻችሁም ስህተት ይሆናሉ፡፡ ሐሳቦችና ስሜቶች ተዋህደው የአንድን ሰው የሞራል ባሕርይ ይመሰርታሉ፡፡ እንደ ክርስቲያን ሐሳባችሁንና ስሜታችሁን ለመቆጣጠር እንደማይጠበቅባችሁ ከወሰናችሁ በክፉ መላእክት ተጽእኖ ሥር ሆናችኋል፤ የእነርሱን መገኘትና ቁጥጥርም እየጋበዛችሁ ነው፡፡ አእምሮአችሁ ለፈጠረው ነገር ከተሸነፋችሁና አስተሳሰባችሁ በጥርጣሬ፣ ባለማመንና በሐዘን መስመር እንዲሄድ ከፈቀዳችሁ ከሟቾች ሁሉ ደስታ የተነፈጋችሁ ትሆኑና ሕይወታችሁ በውድቀት ያከትማል፡፡ Testimonies for the Church vol. 5, p 310. MYPAmh 64.4