መልዕክት ለወጣቶች

52/511

ፈተና ኃጢአት ለመሥራት ምክንያት አይደለም

እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ መንፈሳቸውን የመጠበቅና እጅግ በሚረብሹ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ራሳቸውን የመግዛት እጅግ የተቀደሰ ግዴታ አለባቸው:: በሙሴ ላይ አርፈው የነበሩ ሸክሞች (ሐላፊነቶች) በጣም ትልቅ ነበሩ፡፡ እንደ እርሱ ከባድ ፈተና የሚፈተኑ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ኃጢአት ለመስራት ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሐየር ለህዝቡ በቂ የሆነ ዝግጅት አድርጓል፡፡ በእርሱ ብርታት የሚደገፉ ከሆኑ የሁኔታዎች መጫወቻ አይሆኑም፡፡ ነፍስ እንድትሸከመው የመጣው ፈተና የፈለገውን ያህል ታላቅ ቢሆንም ኃጢአት መስራት ግን የራሳችን ምርጫ ነው፡፡ MYPAmh 47.1

ምድራዊውም ሆነ የገሃነም ኃይሎች ማንንም ሰው ኃጢአት እንዲሰራ የማስገደድ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ሰይጣን በደካማ ጎኖቻቸን በኩል ጥቃት ይሰነዝርብናል፤ ነገር ግን መሸነፍ የለብንም፡፡ ጥቃቱ የፈለገውን ያህል ከባድ ወይም ያልተጠበቀ ቢሆንም እግዚአብሔር እርዳታውን ስለ ሰጠን በእርሱ ብርታት አሸናፊዎች እንሆናለን፡፡ Patriarchs and Prophets p. 421 MYPAmh 47.2