መልዕክት ለወጣቶች
የፍቅር መፈተኛዎች
እያንዳንዷ ወጣት ለጋብቻ እጇን ከመስጠቷ በፊት ለወደፊት ሕይወቷ አንድ ለመሆን የምትፈልገው ሰው የሚገበው መሆኑን መጠየቅ አለባት። ያለፈው ታሪኩ ምን ይመስላል? ሕይወቱ ንፁህ ነውን? የሚገልፀው ፍቅር የከበረና ከፍ ያለ ባሕርይ ያለው ነው ወይስ ዝም ብሎ የስሜት ፍቅር ነው? ሊያስደስታት የሚችል የፀባይ ውርስ አለውን? በፍቅሩ እውነተኛ ሰላምና ደስታ ልታገኝ ትላለችን? የራሷን ማንነት (ግለሰባዊነት) አንድትይዝ ይፈቅድላታል ወይስ ውሳኔዋና ህሊናዋ በባሏ ቁጥጥር ስር እንዲሆን ትደረጋለች? የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደመሆኗ መጠን የራሷ አይደለችም:: በዋጋ ተገዝታለች:: ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማክበር ትችላለችን? ፈቃድና ነፍስ፣ ሃሳብና ተግባር ንፁህና ቅዱስ ሆነው ሊጠበቁ ይችላሉን? እነዚህ ጥያቄዎች ለእያንዳንዷ በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ ልትገባ ላለት ሴት ደህንነት ታላቅ ዋጋ አላቸው። MYPAmh 279.2
በቤት ሐይማኖት ያስፈልጋል። ብዙ ጊዜ የጋብቻ ሕይወትን የሚያመርሩ አሰቃቂ ስህተቶችን የሚከለክል ይህ ብቻ ነው። ጥልቅ፣ እውነተኛና ራስ ወዳድነት የሌለበት ፍቅር ሊገኝ የሚችለው ክርስቶስ በነገሰበት ቦታ ብቻ ነው። ያኔ ነፍስ ከነፍስ ጋር ይጠላለፍና ሁለቱም ነፍሶች በአንድነት ይዋሃዳሉ። የእግዚአብሔር መላእክት በቤቱ ውስጥ በእንግድነት ይገኛሉ። የእነዚህ መላእክት ቅዱስ ጉብኝት የጋብቻውን ክፍል ይቀድሰዋል። ራስን የሚያዋርድ ፍትወት ይጠፋል። ሐሳቦች የሚሳቡት ወደ ላይ ወደ እግዚአብሔር ይሆናል። የልብ መስዋዕት ወደ እርሱ ይነሣል። MYPAmh 279.3