መልዕክት ለወጣቶች

480/511

ከማያምኑ ጋር መተጫጨት

ውድ እህት፦ ከአንቺ ጋር በእምነት አንድ ካልሆነ ሰው ጋር ጋብቻ ለመፈፀም ሀሳብ እንዳለሽ አውቄያለሁ። ይህንን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ በጥንቃቄ አመዛዝነሽ እንዳላየሽ ይሰማኛል። በወደፊት ሕይወትሽ በሙሉ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል እርምጃን ከመውሰድሽ በፊት ጉዳዩን በጥንቃቄና በፀሎት ሆነሽ እንደገና እንድታስቢበት አደፋፍርሻለሁ:: ይህ አዲስ ግንኙት የእውነተኛ ደስታ ምንጭ መሆን ይችላልን? ለክርስትና ሕይወትሽ አጋዥ ይሆንልሻልን? እግዚአብሔርን የሚያስደሰት መሆን ይችላልን? አንቺ ትተሽ የምታልፊው ምሳሌ ሌሎች ያለ አንዳች አደጋ ሊከተሉት የሚችሉት ምሳሌ መሆን ይችላልን? MYPAmh 279.1