መልዕክት ለወጣቶች

455/511

ተጽዕኖ

የክርስቶስ ሕይወት ሁልጊዜ እየሰፋ የሚሄድ፣ ዳርቻ የሌለው፣ እርሱን ከእግዚአብሔርና ከሰብዓዊ ቤተሰብ ጋር የሚያስተሳስር ተጽእኖ ያሳደረ ሕይወት ነው። በክርስቶስ አማካኝነት ሰው ለራሱ ብቻ መኖር እንዳይችል የሚያደርግ ተፅእኖን እግዚአብሔር ሰጥቶታል:: በየግላችን የእግዚአብሔር ታላቅ ቤተሰብ አካል ከሆኑት መሰል ሰዎች ጋር የተገናኘንና የጋራ ግዴታ ያለብን ሰዎች ነን። ማንኛውም ሰው ከሌሎች መሰሎች ተለይቶ ለብቻው መኖር አይችልም! ይህም የሚሆንበት ምክንያት የአንዱ ደህንነት ሌላውንም ስለሚነካ ነው። እያንዳንዳችን ለሌላው ደህንነት አስፈላጊ መሆናችንና ለሌሎች ደስታ መስራት እንዳለብን እንዲሰማን የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። MYPAmh 265.1

እያንዳንዱ ነፍስ በራሱ ከባቢ አየር ተከቦአል! ከባቢ አየሩ ህይወት ሰጭ በሆነ የእምነት፣ የድፍረትና የተስፋ ኃይል የተሞላና በፍቅር መዓዛ የጣፈጠ ወይም በራስ ወዳድነትና እርካታ በማጣት ሐዘን የከበደና የቀዘቀዘ ወይም በተንከባከበው ገዳይ ኃጢአት ግድፈት የተመረዘ ሊሆን ይችላል። ከእኛ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሚከበን ከባቢ አየር ተፅእኖ ሥር ይሆናሉ። MYPAmh 265.2