መልዕክት ለወጣቶች
ታማኝና የሚታመን
ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሆይ፣ ታማኝና የሚታመን ለመሆን ውሳኔው በእጃችሁ ነው። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብትሆኑ ለእውነት ለመቆም ዝግጁና ጽናት ያላችሁ ለመሆን ውሳኔው በእጃችሁ ነው። ትክክለኛ ባህሪያትን ለመመስረት ትሻላችሁን? ፍላጎታችሁ ይህ ከሆነ ጤናማ ግብረገብ ያላቸውንና ዓላማቸው ትክክለኛ ወደ ሆነ ነገር የሚያዘነበሉ ጓደኞችን አብጁ። ውድ የሆነ የምህረት ጊዜ የተሰጣችሁ ከባሕርያችሁ እያንዳንዱን ጉድለት እንድታስወግዱና ይህን ደግሞ ማድረግ የምትፈልጉት የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በዚህ ሕይወትም ጠቃሚ ሰዎች መሆን እንድትችሉ ነው። መልካም ባሕርይ ዋጋው ከወርቅና ከብር የበለጠ ነው። በፍርሃቶችና አለመሳካቶች የሚጠፋ አይደለም! ምድራዊ ሀብቶች በሙሉ ተጠራርገው በሚወሰዱበት ቀን የከበረ ዋጋን ያመጣላችኋል። ታማኝነት፣ ጽናትና ትዕግስት እያንዳንዱ ግለሰብ ለማሳደግ መጣር የሚገባው እሴቶች ናቸው። እነዚህ ነገሮች ባለቤቱን ማንም ሊቋቋም በማይችል ኃይል ያለብሱታል። ያም ኃይል መልካም ለማድረግ፣ ክፉን ለመቃወምና ችግርን ለመሸከም ጠንካራ ያደርጋል። MYPAmh 264.2
የአእምሮ ችሎታን ለማሻሻል ጥቅም ላይ ከሚውሉ ማነሳሻዎች ሁሉ እጅግ ኃይለኛው የእውነት ፍቅርና እግዚአብሔርን ለማስከበር ያለው የሃላፊነት ስሜት ነው። ይህንን ለማድረግ በውስጡ ግፊት ያለው ተማሪ አሿፊ አይሆንም። ሁልጊዜ ከልቡ የሚተጋ ይሆናል። በእግዚአብሔር እይታ ሥር እንዳለና ሰማይ በሙሉ እርሱን በማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርቶ እንዳለ በማወቅ ትምህርቱን ይማራል። በመሆኑም የከበረ አእምሮ ያለው፣ ለጋስ፣ ርህሩህ፣ ገር፣ ክርስቶስን የሚመስልና በሥራው ስኬታማ ይሆናል። ልብና እጅ ከእግዚአብሔር ጋር በመስማማት ይሠራሉ።—Counsels to Parents, Teachers, and Students, 220-226. MYPAmh 264.3