መልዕክት ለወጣቶች

449/511

ኮብላዩ (የጠፋው) ልጅ

የጠፋው ልጅ ትምህርት የተሰጠው ወጣቶችን ለማስተማር ነው። ደስታን በመፈለግና የኃጢአት ተግባራትን በመፈፀም ሕይወቱ ከአባቱ የተቀበለውን ውርስ ከሥርዓት ውጪ በሆነ አኗኗር አባከነ። በባዕድ አገር ወዳጅ የለሽ ነበር። ቡቱቶ ለብሶ፣ ተርቦ ለዓሳማ የሚሰጠውን አሰር ለመመገብ እስከ መመኘት ደረሰ። የመጨረሻ ተስፋው ተቀባይነትንና ይቅርታን ወዳገኘበትና ወደ አባቱ ልብ እንዲጠጋ ወደ ተፈቀደለት የአባቱ ቤት በመፀፀትና ራስን ዝቅ በማድረግ መመለስ ነበር። ብዙ ወጣቶች ልክ ይህ የጠፋው ልጅ እንዳደረገው ሁሉ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሆነውን፣ የእውነተኛ ደስታ ምንጭን በመተው ለራሳቸው ውኃ መያዝ የማይችሉ ሰባራ ጉድጓዶችን በመቆፈር የግድየለሽነትን፣ ደስታን የመሻትንና የብክነትን ህይወት እየኖሩ ናቸው። MYPAmh 260.4