መልዕክት ለወጣቶች

440/511

መደነስ

እውነተኛ የሆነ ክርስቲያን ወደ ማንኛውም የመደሰቻ ቦታ ለመግባት አይሻም፣ ወይም የእግዚአብሔርን በረከት መጠየቅ በማይችልበት በማንኛውም መዝናኛ ላይ አይሰማራም። በቲያትር ቤት፣ በፑል ቤት ወይም በቢሊያርድ አዳራሽ አይገኝም:: ደስታን ፈላጊ ከሆኑ ዘፋኞች ጋር አይተባበርም! ወይም ክርስቶስን ከአእምሮ በሚያስወጣ በማንኛውም አስማት ባለበት መደሰቻ ላይ አይሳተፍም:: MYPAmh 255.1

እንደ እነዚህ ዓይነት መደሰቻዎች እንዲፈቀዱላቸው ለሚማፀኑ ሰዎች መልሳችን በናዝሬቱ በኢየሱስ ስም በእነዚህ መደሰቻዎች መሳተፍ አንችልም የሚል ነው። በቲያትር ወይም በዳንስ ቤት በምናሳልፈው ሰዓት የእግዚአብሔርን በረከት መጠየቅ አንችልም። ማንኛውም ክርስቲያን በእንደዚህ ዓይነት ቦታ መገኘት አይፈልግም። ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ማንኛውም ሰው በዚያ ቦታ መገኘት አይፈልግም። MYPAmh 255.2

ወደ መጨረሻው ሰዓት ስንደርስና ተፅፎ ያለውን የህይወታችንን ታሪክ ፊት ለፊት ስንጋፈጥ በጣም ጥቂት በሆኑ የደስታ ግብዣዎች ላይ በመሳተፋችን እንፀፀት ይሆን? ይልቁንም የራስ ደስታን በማሳደድ ውድ የሆኑ ብዙ ሰዓቶች በመባከናቸው በትክክል ሥራ ላይ ውለው ቢሆን ኖሮ ዘላለማዊ ሀብትን ሊያስገኙልን የሚችሉ ብዙ መልካም አጋጣሚዎች ችላ በመባላቸው አምርረን አንፀፀትምን? MYPAmh 255.3

ሐይማኖተኞች ነን በሚሉ ሰዎች ዘንድ ልባቸው ጋብቻ ለፈፀመው ለማንኛውም አደገኛ መደሰቻ ይቅርታ መስጠት የተለመደ ሆኗል። ኃጢአትን እጅግ ከመለማመዳቸው የተነሣ አሰቃቂ የሆነ ክፋቱን እንዳያዩ ይታወራሉ። ልጆች እንደሆኑ የሚናገሩ ብዙ ሰዎች እርሱ የሌለበትን የስካር ግብዣዎቻቸውን ከአንድ የቤተክርስቲያን በጎ አድራጎት ሥራ ጋር በማገናኘት የእግዚአብሔር ቃል የሚነቅፋቸውን ኃጢአቶች ይደብቃሉ። በመሆኑም ሰይጣንን ለማገልገል የሰማይን ልብስ ይዋሳሉ። ከዚህ የተነሳ ነፍሳት ይታለላሉ፣ ወደ ስህተትም ይመራሉ፣ በዚህ ማራኪ በሆነ ልል ባሕርይ የተነሣም በጎነትንና ታማኝነትን ያጣሉ። MYPAmh 255.4