መልዕክት ለወጣቶች
በሥራ ቦታ ያሉ ያልተቀደሱ ተፅዕኖዎች
በትምህርት ቤቶቻችን ያሉ ወጣቶችን ሚዛናዊ የሆነ አእምሮ እንዲኖራቸው እማፀናቸዋለሁ። በወጣቶች ዘንድ የሚታየው ሞኝነት ለእግዚአብሔር የሚያስደስት አይደለም። የሚጫወቱአቸው ስፖርቶችና የተለያዩ ጨዋታዎች ለፈተና ጎርፍ በር ይከፍታሉ። በአእምሮ ክፍሎቻቸው የሰማያዊ አምላክ ተሰጥኦ ስላላቸው አስተሳሰባቸውን ርካሽና ዝቅተኛ እንዲሆን መፍቀድ የለባቸውም። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ባሉ ጥቅሶች መሰረት የተቀረፀ ባሕርይ ፅኑ መርሆዎችን፣ ንፁህና የከበሩ ፍላጎቶችን ይገልፃል። የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰብዓዊ አእምሮ ኃይሎች ጋር ይተባበራል፣ የዚህም እርግጠኛ ውጤት ከፍ ያለና ቅዱስ ስሜት ይሆናል…። MYPAmh 246.1
ዝቅ ያሉና ተራ የሆኑ የመደሰቻ ግብዣዎች፣ ለመብልና ለመጠጥ፣ ለመዝፈንና የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለመጫወት የሚደረጉ ስብሰባዎች ከምድር በሆነ መንፈስ የተነሳሱ ናቸው። እነዚህ ለሰይጣን የሚቀርቡ መስዋዕቶች ናቸው…። MYPAmh 246.2
በእንደዚህ ዓይነት ከንቱነት የመሪነትን ሚና የሚጫወቱ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ በቀላሉ ሊፋቅ የማይችል ግድፈት ያመጣሉ። የራሳቸውን ነፍሶች ያቆስሉና ጠባሳዎቹን በዕድሜ ልካቸው ይሸከማሉ። ክፉ አድራጊው ኃጢአቱን ሊገነዘብና ሊናዘዝ እግዚአብሔርም ይቅር ሊለው ይችላል! ነገር ግን በተቀደሰውና ተራ በሆነው ነገር መካከል በቀላሉና በፍጥነት የመለየት ኃይል በከፍተኛ ደረጃ ይበላሻል። Counsels to Teacher, Parents and Students, P. 366-368. MYPAmh 246.3