መልዕክት ለወጣቶች

414/511

በትንንሽ ነገሮች ታማኝ መሆን

የግል፣ የማያቋርጥ፣ የተባበረ ጥረት በክንዋኔ ይሸለማል። በዓለማችን ውስጥ የጎላ መልካም ነገር ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ትናንሽ ነግሮችን በማከናወን እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ለመፈፀም ፍቃደኛ መሆን አለባቸው። አንድ ታላቅና አስደናቂ ነገር በማድረግ ወደ ስኬት ከፍታዎች መድረስ የሚፈልግ ሰው ምንም ነገር ሳያደርግ ይቀራል። MYPAmh 239.3

በጥሩ ስራ የማያቋርጥ ለውጥ ማሳየት፣ አንድ አይነት የታማኝነት አገልግሎት ሁል ጊዜ መደጋገም በእግዚአብሔር እይታ አንድ ታላቅ ስራ ከመስራት የበለጠ ዋጋ አለው። ወጣቶች ለሚያደርጉት ጥረቶች መልክ በመስጠት መልካም ሪፖርት ያስገኝላቸዋል። MYPAmh 239.4

ወጣቶች ነፍሳትን ለማዳን በመስራት መልካም ማድረግ ይችላሉ። የተሰጡአቸውን መክሊቶች ስራ ላይ ማዋል አለማዋላቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንደሆኑ የሚናገሩ ሁሉ ከፍ ወዳለው ደረጃ ያልሙ። እግዚአብሔር የሰጣቸውን እያንዳንዱን የአካል ክፍል ይጠቀሙ። The youth’s Instructor, January 1, 1907. MYPAmh 239.5