መልዕክት ለወጣቶች
የጥበብ መንገድ
ብዙ ጊዜ ወጣቶች እንደ እርሾ በመሆን አእምሮን የሚቀይር ነገር ያስፈልገናል ይላሉ። የሚያስፈልገው ነገር የክርስቲያን ተስፋ ነው። ሐይማኖት ለአማኝ አፅናኝና ወደ እውነተኛ የደስታ ምንጭ የሚመራ እርግጠኛ መሪ ነው። ወጣቶች በተመስጦና በጸሎት የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት አለባቸው። ይህንን ሲያደርጉ ትርፍ ጊዜያቸውን ከዚህ ለተሻለ ነገር መዋል እንደማይችል ያውቃሉ። «የጥበብ መንገዶች ምቹ መንገዶች ናቸው፣ መንገዶችዋም በሙሉ ሰላም ናቸው።» MYPAmh 238.4
ጳውሎስ ለቲቶስ በጻፈው መልእክቱ ወጣቶች ራሳቸውን የሚገዙ እንዲሆኑ ይመክራል። “እንዲሁም ወጣቶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው። የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፣ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፣ ጭምትነትን፣ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።” MYPAmh 238.5
ወጣቶች ለነፍሳቸው በማለት የሐዋርያውን ምክር እንዲሰሙ አደፋፍራቸዋለሁ። እነዚህ ፀጋ ያለባቸው ትምህርቶች፣ ማስጠንቀቂያዎችና ተግሣፆች የሕይወት ሽታ ለሕይወት ወይም የሞት ሽታ ለሞት ሊሆኑ ይችላሉ። MYPAmh 238.6
ወጣቶች በተፈጥሮአቸው ብዙ ኃላፊነት፣ ጥንቃቄ ማድረግና ሸክም መሸከም እንደማይጠበቅባቸው ወደ ማሰብ ያዘነብላሉ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን መስፈርት የማሟላት ግዴታ አለበት። በተለያዩ አጋጣሚዎችና ልዩ እድሎች፣ በቃል አገልግሎት፣ በምክሮች፣ በማስጠንቀቂያዎችና በተግሣፆች አማካኝነት የሚበራው ብርሃን ባሕርይ ፍፁም እንዲሆን ያደርጋል፣ ወይም ግድ የለሹን ይኮንነዋል። ወጣቶችም ሆኑ በእድሜ የገፉ ይህንን ብርሃን በልባቸው ማስቀመጥ አለባቸው:: በሕይወታቸው ለእግዚአብሔር አገልግሎት ቅድሚያ ለመስጠት በመወሰን ከእርሱ ጋር ለመቆም ውሳኔ የሚያደርጉ እነማን ናቸው? ሸክም ተሸካሚዎች እነማን ይሆኑ ይሆን? MYPAmh 238.7
“በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ።» ኢየሱስ በላያቸው የወጣትነት ጤዛ ያለባቸውን ግለሰቦች አገልግሎት ይሻል። ዘላለማዊነትን የሚወርሱ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ብዙ ወጣቶችን በልጅነት እድሜያቸው እያበላሸ ያለ የግብረ ገብ ብክለት መብዛት ቢታወቅም ወደ ከበረ ሙሉ ወንድነትና ሙሉ ሴትነት ማደግ ይችላሉ። በክርስቶስ ነፃ፣ የጨለማ ሳይሆን የብርሃን ልጆች መሆን ይችላሉ። MYPAmh 239.1
እግዚአብሔር እያንዳንዱን ወጣት ወንድና እያንዳንዷን ወጣት ሴት እያንዳንዱን ክፉ ባሕርይ እንዲተዉ፣ በተግባራቸው ትጉህ እንዲሆኑና ጌታን በማገልገል በመንፈስ የጋሉ እንዲሆኑ ይጠራቸዋል። መጥፎ ልምዶችን ለማሸነፍ ወይም ባሕርይን ለማሻሻል ምንም ጥረት ሳያደርጉ በግድየለሽነት ውስጥ መቆየት የለባቸውም:: ፀሎታቸው ከልባቸው መሆኑ የሚረጋገጠው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመታዘዝ በሚያደርጉት ብርቱ ጥረት ነው። ጌታ በመንፈሱ የማሸነፍን ኃይል እንደሚሰጣቸው በማመን በእያንዳንዱ እርምጃ መጥፎ ልምዶችንና ጓደኞችን •እየተዉ ይሄዳሉ። MYPAmh 239.2