መልዕክት ለወጣቶች
ክፍል 13 — መዝናኛና መደሰቻ
በመዝናኛና በመደሰቻ መካከል ልዩነት አለ። መዝናናት ቃሉ እንደሚገልፀው ሁሉ አካልን የማበረታታትና የመገንባት ሂደት ነው። ከተራ የዕለት ተግባሮቻችን በመለየት ለአካላችንና ለአእምሮአችን መታደስን ይሰጣል። በመሆኑም ወደ ሕይወት ተግባራችን በአዲስ ብርታት እንድንመለስ ያደርገናል። መደሰቻ በተቃራኒው ደስታን ለመፈለግ ብቻ ተብሎ የሚደረግና ብዙ ጊዜ ከሚያስፈልገው በላይ የሚሄድ ነው። ለጠቃሚ ሥራ የሚውለውን ኃይል በሙሉ ይመጥና ለእውነተኛው የሕይወት ክንውን እንቅፋት ይሆናል። Education, P. 207. MYPAmh 235.1