መልዕክት ለወጣቶች

405/511

ዓለምን መከተል

ፋሽንን በተመለከተ የዓለምን መዝቀጥ በመመልከት ክርስቲያን ነን ባዮች እንዴት የዓለምን መንገድ ለመከተል እንደፍራለን? እነዚህን አዋራጅ ፋሽኖችን ወደ እኛ በማስገባት ትክክል እንደሆነ ማረጋገጫ እንሰጣለንን? ብዙዎች ፋሽንን የሚቀበሉበት ምክንያት የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በውስጣቸው ስላልተመሰረተ ነው። የቅንጦት ኑሮ፣ ከመጠን ያለፈ የአለባበስ ብክነት ከመጨረሻው ዘመን ምልክቶች አንዱ እስከ መሆን ድረስ ተፈፃሚ እየሆነ ነው። MYPAmh 233.3

በየቦታው ኩራትና ከንቱነት ይታያሉ። ራሳቸውን ለማድነቅ መስታወትን ለማየት የሚያዘነብሉ ሰዎች ወደ ታላቁ የግብረገብ መስታወት ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ህግ ለማየት ዝንባሌ የላቸውም። የልብስ ጣኦት በባህሪይ ውስጥ ያለውን ትሁት፣ የዋህና ውብ የሆነውን ነገር ሁሉ ያጠፋል። በእግዚአብሔር ፊት ለፀጥታ፣ ልብን ለመመርመርና በፀሎት ቃሉን ለማጥናት መዋል ያለባቸውን ውድ ሰዓቶች ይበላል። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለእኛ ለትምህርታችን የሚሆኑ ነገሮችን የእግዚአብሔር መንፈስ አስቀምጦልናል። MYPAmh 233.4

ለአለባበስ ራስን መስጠት ለምህረትና ለልግስና ሥራ ከተሰጠን ገንዘብ ይወስድብናል። ይህ ብክነት ያለበት አጠቃቀም እግዚአብሔርን መቀማት ነው። ሐብት የተሰጠን የኩራትና የታይታ ፍቅራችንን እንድናረካ አይደለም። ብልህ መጋቢዎች በመሆን የተራቆቱትን ማልበስ፣ የተራቡትን መመገብና ንብረታችንን ለእግዚአብሔር ሥራ ማዋል አለብን። ውበትን ከፈለግን የየዋህነት፣ ራስን ዝቅ የማድረግ፣ የጨዋነትና የጥንቁቅነት ፀጋዎች ለማንኛውም ሰው፣ በየትኛውም የኑሮ ደረጃና የሕይወት ሁኔታ ውስጥ ላለ ሁሉ ገጣሚ ነው። MYPAmh 233.5

እንደ ታማኝ ወታደር በዘመናችን እየሆነ ያለውን የግብረ ገብ ውድቀትንና ብክነትን ለመቃወም በቃልና በሕይወት ምሳሌነት አቋማችንን አንገልጥምን? ብንበላ ወይንም ብንጠጣ ወይንም ማንኛውንም ነገር ብናደርግ ሁሉንም ለእግዚአብሔር ክብር በማድረግ ለወጣቶቻችን ትክክለኛ ምሳሌ አንተውላቸውምን? Review and Herald December 12, 1912. MYPAmh 233.6