መልዕክት ለወጣቶች
ከፋሽን ጋር ያለው ግንኙነት
ክርስቲያኖች የተለየ አለባበስ በመልበስ ራሳቸውን የሚታይ ዕቃዎች ለማድረግ መጣር የለባቸውም፡፡ ነገር ግን እንደ እምነታቸውና ተግባራቸው ጨዋነት ያለበትንና ጤናማ የሆነ አለባበስን ቢከተሉ ኖሮ ራሳቸውን ከፋሽን ውጭ ሆነው ያገኙ ነበር፤ አለባበሳቸው መቀየር ያለበት ዓለምን ለመምሰል መሆን የለበትም፡፡ ነገር ግን ዓለም በሙሉ ከእነርሱ ቢለይም ትክክለኛ ለመሆን፣ ከጥገኝነት ነጻ የሆነ የከበረ ባሕርይንና የሞራል ድፍረትን ማሳየት አለባቸው፡፡ ዓለም ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚስማማ ጨዋ የሆነ፣ ምቹና ጤናማ አለባበስን ቢያመጣና ያንን ዓይነት አለባበስ ክርስቲያኖችም ብንከተል ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት አይለውጥም፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስን መከተል አለባቸው፡፡ የሌሎችን ሙገሳም ሆነ ነቀፌታን ሳይፈሩ በትህትና ትክክለኛውን መንገድ መከተል አለባቸው፡፡ ትክክለኛ ከሆነ ነገር ጋር ትክክል ከመሆኑ የተነሣ መጣበቅ አለባቸው፡፡ Review and Zerald, January, 30,1900. MYPAmh 226.4