መልዕክት ለወጣቶች

391/511

አለባበስና ባሕርይ

የክርስቶስ ተከታዮች እንደ ምድር ጨውና እንደ ዓለም ብርሃን ተመስለዋል፡፡ ያለ ክርስቲያኞች የማዳን ተጽዕኖ ዓለም በራሱ ኃጢአት ይጠፋል፡፡ ስለ አለባበሳቸውና ማንነታቸው ግድ የሌላቸውን ክርስቲያን ነን ባዮች ተመልከቱአቸው፡፡ አለባበሳቸው እንደሚወክለው ሁሉ በሥራቸውም የማይታመኑ ናቸው፡፡ በባሕርያቸው ያልተሞረዱ፣ ትህትና የጎደላቸውና ሸካራዎች ናቸው፡፡ በንግግራቸውም እጅግ የወረዱ ናቸው፡፡ ሆኖም እነዚህን አሳዛኝ ባሕርያት እንደ እውነተኛ ራስን ዝቅ ማድረግና ክርስቲያናዊ ሕይወት ይቆጥሩታል፡፡ አዳኛችን ዛሬ በምድር ላይ ቢኖር ኖሮ እነዚህን የምድር ጨውና ብርሃን ናቸው ብሎ ያሳይ ይሆን በፍጹም አያደርገውም! MYPAmh 226.1

ክርስቲያኖች በንግግራቸው የከበሩ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የውሸት ሙገሳን ኃጢአት እንደሆነ የሚያምኑ ቢሆኑም ትሁት፣ ቸርና ለጋስ ናቸው፡፡ ቃላቶቻቸው ማስመሰል የሌለባቸውና እውነት ናቸው፡፡ ከወንድሞቻቸውና ከዓለም ጋር ባላቸው ግንኙነት ታማኝ ናቸው፡፡ በአለባበሳቸው ራስን ከፍ ማድረግንና ታይታን ይሸሻሉ፡፡ ነገር ግን ልብሶቻቸው ንጹህ፣ ጨዋነትን የተላበሱ፣ በለባሹ ላይ ሲታዩ በትክክል የሚገጥሙና የሚያምሩ ናቸው፡፡ ለተቀደሰው ሰንበትና ለቅዱስ አምልኮ ያለንን ቅዱስ አክብሮት በሚገልጽ መንገድ ልብሶቻችንን ለመልበስ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡በእነዚህ ክርስቲያኖችና በዓለም መካከል ያለው ልዩነት መሳሳት እስከማይቻል ድረስ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ MYPAmh 226.2

በፊት በባሕርያቸው ግድ የለሾችና ልል የነበሩ አሁን ግን እውነትን የተቀበሉ ወንዶችና ሴቶች በአለባበሳቸው ንጽህናን፣ ሥነ ሥርዓትንና ለዛ ያለው አለባበስን ባሕርያት ለመከተል በእውነት ሲቀደሱና ሲከብሩ የእነርሱ በሌሎች ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ አሥር እጥፍ ነው፡፡ አምላካችን የሥነ ሥርዓት አምላክ ነው፡፡ እርሱ የፈለገው ነገር ቢሆን፣ ሥርዓት በጎደለው ነገር፣ ንጽህና በሌለው ነገር ወይም በኃጢአት አይደሰትም፡፡ MYPAmh 226.3