መልዕክት ለወጣቶች
ቤትን የደስታ ቦታ ማድረግ
እነዚህ ወጣቶች በረከት መሆን ያለባቸው ቦታ ካለ በቤት ውስጥ ነው፡፡ መመራት በሚገባቸው ጥንቃቄ በተሞላና ባልተበላሸ አስተሳሰብ፣ ጤናማ ግንዛቤና በተማረ ህሊና ከመመራት ይልቅ ለዝንባሌ የሚሸነፉ ከሆነ ለህብረተሰቡም ሆነ ለአባታቸው ቤት በረከት መሆን አይችሉም፡፡ ከዚህ የተነሣ በዚህ ዓለምም ሆነ ከዚህ በሚሻለው ዓለም ለስኬት ያላቸው ተስፋ አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡• MYPAmh 219.3
ብዙ ወጣቶች የወጣትነት ጊዜያቸውን በስፖርት፣ በፌዝ፣ በቀልድና በማይጠቅሙ ደስታ ማግኛዎች ለማሳለፍ እንጂ ኃላፊነት ለመሸከም የተዘጋጁ እንዳልሆነ ግንዛቤ ይይዛሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሞኝነትና የስሜትን ፈቃድ በመፈጸም ላይ ያሉ አንዳንዶች ከዚህ ጋር የተገናኘውን ጊዜያዊ ደስታ እንጂ ሌላ ምንም ነገር አያስቡም፡፡ ለደስታ ያላቸው ፍላጎት፣ ከሌሎች ጋር አብሮ ለመሆን፣ ለማውራትና ለመሳቅ ያላቸው ፍቅር እየጨመረ ይሄድና ሰላማዊ ለሆኑት የሕይወት እውነታዎች ፍላጎት ከማጣታቸው የተነሣ የቤት ውስጥ ሥራዎች የማያስደስቱ ይመስላሉ፡፡ ለአእምሮአቸው የሚገጥም በቂ ለውጥ ስለሌለ እረፍት የለሾችና በቀላሉ የሚረበሹ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች ቤትን ደስታና ፍስሃ ያለበት ማድረግ ተግባራቸው እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ MYPAmh 219.4
ጉልበትን ከሚጠይቅ ሥራ ጊዜያዊ ለውጥ አስፈላጊ ነው፤ ይህም የበለጠ ስኬተን የሚያመጣ ሥራ ላይ ለመሰማራት ኃይልን ለማሰባሰብ ይረዳል፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከሥራ ማረፍ አስፈላጊ አይደለም…፡፡ MYPAmh 219.5
አንድ አይነት ሥራን መስራት ሲደክማቸው እንኳን ውድ ጊዜያቸውን በከንቱ ማሳለፍ የለባቸውም፡፡ በዚያን ጊዜ አድካሚ ያልሆነ ለእናታቸውና ለእህቶቻቸው በረከት መሆን የሚችል ነገር ለማድረግ መሻት ይችላሉ፡፡ ሊሸከሙአቸው የሚገቡትን ከባድ ሸክሞች በመሸከም ኃላፊነታቸውን በሚያቀሉበት ጊዜ ከትክክለኛ መርህ የሚገኘውን ደስታ ማግኘት ይችላሉ፣ እርሱም እውነተኛ ደስታ ይሰጣቸዋል፤ ጊዜያቸውም በከንቱ ንግግርና የራስ ደስታ በመሻት አይባክንም፡፡ Testimonies for the Church, vol. 3, P. 221-223. MYPAmh 219.6