መልዕክት ለወጣቶች
የወጣቶች ሐላፊነትን ለመሸከም መጠራት
(ለሁለት ወጣቶች የተሰጠ መልዕክት)
እነዚህ ወጣቶች በቤታቸው ውስጥ ችላ ያሉአቸው ተግባሮች አሉ፡፡ ሊሸከሙአቸው የሚገባውን በቤት ውስጥ ያሉ ኃላፊነቶችን እንዲሸከሙ አልተማሩም፡፡ ልጆች ብቻዋን እንድትሸከም ዝም ሊሏት የማይገባ ብዙ ሸክሞችን የተሸከመች ታማኝና ታታሪ እናት አለችላቸው፡፡ በዚህ ረገድ እናታቸውን አላከበሩአትም፡፡ የአባታቸውን ሸክሞች እንደ ኃላፊነት ቆጥረው አልተጋሩም፤ ይህንን በማድረጋቸው ማክበር የሚገባቸውን ያህል አላከበሩትም፡፡ ከተግባር ይልቅ ዝንባሌያቸውን ይከተላሉ፡፡ MYPAmh 219.1
በሕይወታቸው የራስ ወዳድነትን መንገድ ተከትለዋል፣ ሸክም መሸከምንና ልፋትን በመሸሽ በሕይወታቸው ስኬትን ለማግኘት ከፈለጉ ሊያጡት የማይገባውን ጠቃሚ ልምምድ ሳያገኙት ቀርተዋል፡፡ በትናንሽ ነገሮች ታማኝ ሆኖ የመገኘት አስፈላጊነት አልተሰማቸውም፣ እንደዚሁም በመንገዳቸው ላይ ያሉትን ዝቅ ያሉና አነስተኛ ተግባራትን ለወላጆቻቸው የመፈጸም ግዴታ እንዳለባቸው አልተሰማቸውም፡፡ ለተግባራዊ ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ወደሆኑ ከተለምዶ የእውቀት ዘርፎች በላይ ይመለከታሉ፡፡ MYPAmh 219.2