መልዕክት ለወጣቶች

349/511

በአለባበስ ቁጠባ

የእግዚአብሔር ህዝቦች በንብረት አጠቃቀማቸው ላይ ለእግዚአብሔር “ያንተው ከሆነው ለአንተው እንሰጣለን::» ብለው ለማምጣት የሆነ ነገር እንዲኖራቸው ጥብቅ ቁጠባን መለማመድ አለባቸው። ከእግዚአብሔር ለተቀበሉአቸው በረከቶች የምስጋና ሥጦታ መስጠት አለባቸው። ለራሳቸው ደግሞ በእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ ሐብት ማከማቸት አለባቸው። MYPAmh 202.1

አለማውያን በረሃብና በብርድ እየተሰቃዩ ያሉትን የሚመግብንና የሚያለብስን ብዙ ገንዘብ በልብስ ላይ ያባክናሉ። ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ማብቂያ የሌላውን የፋሽን ፍላጎት ለማሟላት እያባከኑ ሳሉ ክርስቶስ ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላቸው ብዙዎች ግን እጅግ ርካሽና ተራ የሆኑ ልብሶች እንኳን የላቸውም። MYPAmh 202.2

ጌታ ህዝቡ ከዓለም እንዲወጡና የተለዩ እንዲሆኑ ነግሯቸዋል። የምህረት ዘመን ፍፃሜ ላይ ስለምንኖር ለሚያምኑ ሰዎች ያሸበረቁና ውድ ልብሶችን መልበስ ተገቢ አይደለም። ሐዋሪያው ጰውሎስ ስለ አለባበስ እንደሚከተለው ጽፎታል፡- “እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ ያለ ቁጣና ያለ ክፉ ሃሳብ የተቀደሱትን እጆች በማንሳት እንዲፀልዩ እፈቅዳለሁ። እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ! እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉ ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በእንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ::” 1ኛ ጢሞ፡ MYPAmh 202.3

የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ በሚናገሩት መካከል እንኳን በልብስ ላይ ከሚያስፈልገው በላይ ወጪ የሚያደርጉ ሰዎች አሉ። ንፁህና ለዛ ያለው አለባበስ ሊኖረን ይገባል፣ ነገር ግን እህቶች ሆይ፣ የራሳችሁንና የልጆቻችሁን ልብስ ስትገዙና ስትሰሩ በጌታ የወይን ቦታ ሊሰራ እየጠበቀ ያለውን ሥራ አስቡ። ጥሩ ነገር መግዛትና በጥንቃቄ ማሠራት ትክክል ነው። ይህ ቁጠባ ነው። ነገር ግን ውድ መጋጌጫዎች አስፈላጊ አይደሉም ፣ እነዚህን ነገሮች ማድረግ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ መዋል የሚችለውን ገንዘብ ለራስ ደስታ ማዋል ነው። MYPAmh 202.4

በእግዚአብሔር እይታ ዋጋ የሚያሰጣችሁ ልብሳችሁ አይደለም። እግዚአብሔር ዋጋ የሚሰጠው ለውስጣዊ ውበት፣ የመንፈስ ፀጋዎች፣ ትሁት ቃላትና ለሌሎች ያላችሁን አሳቢነት ነው። አለአስፈላጊ መጋጌጥን አስወግዱና ለዚያ የሚውለውን ገንዘብ የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ተጠቀሙበት። MYPAmh 202.5