መልዕክት ለወጣቶች
ለእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች
የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉ ሁሉ በየዓመቱ በተለይም አመታዊ በዓላት በመጡ ቁጥር በራስ ወዳድነት የተሞሉና ቅዱስ ያልሆኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት፣ የምግብ ፍላጎትን ለማርካትና ክርስቲያናዊ ባልሆነ ታይታ ከሌሎች ጋር ለመወዳደር ምን ያህል እንደሚያወጡ ያስሉ። ስለዚህ በማያስፈልግ ሁኔታ የባከነውን ገንዘብ ደምሩና በአካልና በነፍስ ላይ ጉዳት ሳይደርስ ለእግዚአብሔር ሥራ እንደ ቅዱስ ሥጦታ ምን ያህል ገንዘብ ማዳን እንደሚቻል ገምቱ። MYPAmh 201.4
አነስተኛም ቢሆኑ የልግሥና ሥጦታዎች እንደ ሰጪው ችሎታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ቤተ ክርስቲያናትን እዳ ለማንሳት ሊመጡ ይችላሉ። ወደ አዳዲስ መስኮች የሚላኩ ሚስዮናውያን ይኖራሉ፣ ሌሎች ደግሞ በሚሰሩበት የሥራ መስኮች ይረዳሉ። እነዚህ ሚስዮናውያን ደግሞ እናንተ በየቀኑ የምትደሰቱባቸውን ነገሮችና ለሕይወት አስፈላጊ እንደሆኑ የምትገምቱአቸውን ነገሮች ለራሳቸው በመንፈግ ጥብቅ ቁጠባን መለማመድ አለባቸው:: እነርሱ ቅንጦታቸው አነስተኛ ነው። Review and Herald, Nov. 21,1878. MYPAmh 201.5