መልዕክት ለወጣቶች

338/511

የእግዚአብሔርን ባለቤትነት እውቅና መስጠት

ከትርፋችን ሁሉ ከአትክልትም ሆነ ከእርሻ፣ ወይም ከመንጋዎቻችን ወይም ከአእምሮ ወይም ከጉልበት ሥራ ከሚገኝ ገቢ ለእግዚአብሔር አስራትን ቀድሶ መስጠት፣ ሁለተኛውን አስራት ደግሞ ለድሆች እርዳታ ወይም ለማንኛውም የበጎ አድራጎት ስራ መጠቀም በሰዎች ፊት የእግዚአብሔርን የሁሉም ነገር ባለቤትነት እንዲያዩ ለማድረግና እነርሱም የበረከቱ መተላለፊያ መንገዶች የመሆን እድል እንዳላቸው ለማሳየት የታቀደ ነው። ጠባብነትን የሚያመጣውን እራስ ወዳድነትን በሙሉ ለመግደልና የባሕርይ ስፋትንና ክቡርነትን ለማሳደግ የተዘጋጀ ሥልጠና ነበር። Education, P. 44. MYPAmh 197.4