መልዕክት ለወጣቶች

337/511

አሥራት

ኢየሱስ ለመፈፀም የመጣበት ታላቅ ስራ ኃላፊነት የተሰጣቸው በምድር ለነበሩ ተከታዮቹ ነበር። ክርስቶስ በታላቁ የደህንነት ሥራ ውስጥ የእኛ እራስ ሆኖ ይመራና እኛ የእርሱን ምሳሌ እንድንከተል ይጠይቀናል። ዓለም አቀፋዊ መልዕከት ሰጥቶናል። ይህ እውነት ለህዝብ፣ ለቋንቋ፣ ለነገድ ሁሉ መድረስ አለበት። ከሰይጣን ኃይል ጋር ትግል ተገጥሞ በክርስቶስና በተከታዮቹ መሸነፍ አለበት። ከጨለማ ኃይላት ጋር መጠነ-ሰፊ ጦርነት መደረግ አለበት። ይህንን ስራ በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ። ለዚህ የሚያስፈልጉ ነገሮችን እግዚአብሔር ከሰማይ በቀጥታ ለመላክ ሃሳብ አልሰጠም፣ ነገር ግን ይህንን ጦርነት በድል ለመወጣት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ወይም መክሊቶችን በተከታዮቹ እጆች ይሰጣል። MYPAmh 197.1

ሥራው ራሱን እንዲችል የሚያደርግ በቂ ገንዘብ እንዲሰበስቡ ጌታ ለሕዝቡ እቅዱን ሰጥቷቸዋል። በአስራት አከፋፈል ላይ ያለው የእግዚአብሔር እቅድ በቀላልነቱም ሆነ በእኩልነቱ የሚያምር ነው። መሰረቱ መለኮታዊ ስለሆነ ሁሉም በእምነትና በድፍረት አጥብቀው ሊይዙት ይችላሉ። በእርሱ ውስጥ ትህትናና ጠቃሚነት የተቀላቀሉበት ስለሆነ ለመርዳትና ለመተግበር ጥልቅ ትምህርትን አይጠይቅም:: የደህንነትን ውድ ስራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ለማድረግ ሁሉም የራሳቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚችሉ ሊሰማቸው ይችላል። እያንዳንዱ ሰው፣ ሴትና ወጣት ለጌታ ግምጃ ቤት መሆንና በግምጃ ቤቱ ውስጥ የሚፈለገውን ነገር ለማሟላት ወኪል መሆን ይችላል። ጳውሎስ «እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር ባዘዘው መጠን በጎተራው አስቀምጡ” ይላል:: MYPAmh 197.2

በዚህ መንገድ ታላላቅ ስራዎች ተሰርተዋል። አንድም ሆነ ሁሉም ቢቀበሉት ኖሮ እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር ንቁና ታማኝ ግምጃ ቤት መሆን ይችል ነበር። ለዓለም ሊሰጥ ያለውን የመጨረሻውን ማስጠንቀቅያ መልእክት የማስተጋባት ታላቅ ሥራን ወደ ፊት ለማስቀጠል የገንዘብ እጥረትም አይገጥምም ነበር። ሁሉም ይህን መንገድ ቢቀበሉ ኖሮ ግምጃ ቤቱም ሙሉ ይሆን ነበር! ሰጪዎቹም ደሃ እንዲሆኑ አይተዉም ነበር። በእያንዳንዱ በሚሰጡት መጠን ለወቅቱ እውነት ሥራ የበለጠ እጩዎች ይሆኑ ነበር። “ሊመጣ ካለው ጊዜ ለመጠበቅና የዘላለምን ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ለራሳቸው በላይ ጥሩ መሰረት ያለው መዝገብ እያከማቹ ናቸው።” Testimonies for the Church, Vol. 3, P. 388-389. MYPAmh 197.3