መልዕክት ለወጣቶች

329/511

በቁጠባ ላይ የተሰጡ ትምህርቶች

ወጣቶች የቁጠባንና እራስን የመካድን ትምህርቶች በመማር የእግዚአብሔርን ስራ ለመርዳት ስላላቸው መልካም እድል ብዙ ሊባል ይችላል። ብዙዎች መደሰት እንዳለባቸው ስለሚያስቡ ያንን እንዲያደርጉት የተሰጣቸውን ገቢ በሙሉ ለራሳቸው መጠቀምን ይለማመዱታል። በዚህ ረገድ የተሻለ ነገር እንድንሰራ ጌታ ይጠብቅብናል። MYPAmh 194.1

ለመብላት፣ ለመጠጣትና ለመልበስ በቂ በሆነ ነገር ብቻ ረክተን ስንቀመጥ በራሳችን ላይ ኃጢአትን እየሰራን ነን። እግዚአብሔር ከዚህ ከፍ ያለ ነገር በፊታችን አለው። የራስ ወዳድነት ፍላጎቶቻችንን ለመጣል ፈቀደኞች ስንሆንና የልብንና የአእምሮን ኃይሎች ለእግዚአብሔር ስራ ስንሰጥ ሰማያዊ ወኪሎች ከእኛ ጋር በመተባበር ለሰብዓዊ ዘር በረከት እንድንሆን ያደርጉናል። MYPAmh 194.2