መልዕክት ለወጣቶች

302/511

የመጻሕፍት መጽሐፍ

የአንድ ሰው ሃይማኖታዊ ልምምድ የሚገለፀው ግለሰቡ በትርፍ ጊዜው ለማንበብ በሚመርጣቸው መጽሐፍት በህሪይ ነው። ጤናማ የሆነ አእምሮና መንፈሳዊ መርህ እንዲኖራቸው ወጣቶች በቃሉ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እያደረጉ መኖር አለባቸው። በክርስቶስ አማካኝነት የደህንነትን መንገድ በማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ከፍ ላለ እና ለተሻለ ሕይወት መመሪያችን ነው። እስከ ዛሬ ከተፃፉት መጻሕፍት ሁሉ የተሻለ እጅግ ተወዳጅና አስተማሪ የሆነ ታሪክና የሕይወት ታሪክ ይዟል። ልብ ወለድን በማንበብ አስተሳሰባቸው ያልተዛባ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከመጻሕፍት ሁሉ ተወዳጅ ሆኖ ያገኙታል። MYPAmh 179.3

መጽሐፍ ቅዱስ የመጻሕፍት መጽሐፍ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ብትወዱና በውስጡ ያለውን ሀብት የራሳችሁ ለማድረግ እንድትችሉና ለመልካም ሥራ ሁሉ የተዘጋጃችሁ መሆን እንድትችሉ በአገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ብትመረምሩ ኢየሱስ ወደ ራሱ እየሳባችሁ ለመሆኑ እርግጠኞች መሆን ትችላላችሁ። ትምህርቱን ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ሳይሆን ቃሉን በተለምዶአዊ ሁኔታ ማንበብ ከክርስቶስ ፈቃድ ጋር መስማማት እንድትችሉ ለማድረግ በቂ አይደለም። በእውነት ቁፉሮ ቦታ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መቆፈሪያውን አጥልቀን በማስገባት ብቻ የሚገኙ ሀብቶች አሉ። MYPAmh 179.4

ሥጋዊ አእምሮ እውነትን አይቀበልም። ነገር ግን የተለወጠ ነፍስ አስደናቂ ለውጥ ውስጥ ያልፋል። ከዚህ በፊት በኃጢአተኛው ላይ ምስክር የሚሆኑ እውነቶችን በመግለፁ ምክንያት ይጠላ የነበረው መጽሐፍ አሁን የነፍስ ምግብ፣ የሕይወት ደስታና መጽናኛ ይሆናል። የጽድቅ ፀሐይ የተቀደሱ ገፆችን ያበራና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ አማካኝነት ለነፍስ ይናገራል። MYPAmh 179.5

ከዚህ በፊት የቀላል ንባቦች ፍቅር ያጎለበቱ ሁሉ አሁን ትኩረታቸውን ወደ እርግጠኛው የትንቢት ቃል ይመልሱ። መጽሐፍ ቅዱሶቻችሁን ውሰዱና የብሉይንና የአዲስ ኪዳንን ቅዱስ መዛግብት በአዲስ ፍላጎት ማጥናት ጀምሩ። መጽሐፍ ቅዱስን ቶሎ ቶሎና በትጋት በአጠናችሁት ቁጥር ውበቱ እየጨመረ ይሄድና ለቀላል ፅሁፎች ያላችሁ ፍላጎት እየቀነሰ ይሄዳል። ይህን ውድ መጽሐፍ በልባችሁ እሰሩት። ወዳጃችሁና መሪያችሁ ይሆንላችኋል። The Youth’s Instructor, October 9, 1902. MYPAmh 179.6