መልዕክት ለወጣቶች

301/511

የመንፈሳዊነት ጠላቶች

ታትመው ካሉ መፅሀፍት አብዛኛቹ የሚጠፉ ቢሆን ኖሮ በአእምሮና በልብ ውስጥ አስፈሪ ስራን እየሰራ ያለ መቅሰፍት ይታገድ ነበር። የፍቅር ታሪኮች፣ ከንቱና ስሜትን የሚቀሰቅሱ አፈ ታሪኮችና መንፈሳዊ ልብ ወለድ ተብለው የሚመደቡ መፅሀፍትም ቢሆኑ (ደራሲው ከራሱ ታሪክ ጋር የግብረ ገብ ትምህርትን የሚያያይዝባቸው መጻሕፍቶች) ለአንባቢዎቹ እርግማን ናቸው። በመጽሐፉ ውስጥ በአጠቃላይ ሃይማኖታዊ ስሜት ተጠላልፎበት ሊሆን ይችላል! ነገር ግን በአብዛኛው ሰዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማታለል እንዲያመቸው ሰይጣን በመልአክ ልብስ ተሸፍኖ የሚመጣበት መንገድ ነው። እነዚህን ታሪኮች እያነበበ እያለ ሙሉ በሙሉ ችግር እስከማይገጥመው ድረስ ከፈተና ነፃ የሆነና በእውነተኛ መርህ ላይ የጸና ማንም የለም። MYPAmh 178.4

የልበ-ወለድ አንባቢዎች የተቀደሱ ገፆችን ውበት በመጋረድ መንፈሳዊነትን የሚያጠፋን ክፋት እየፈፀሙ ናቸው። ጤናማ ያልሆነ የስሜት መቀስቀስን ይፈጥራል፣ አስተሳሰብን ያተኩሳል፣አእምሮን ለጠቃሚ ነገር ገጣሚ እንዳይሆን ያደርጋል፣ ነፍስን ከፀሎት በመለየት ለማንኛውም መንፈሳዊ ሥራ ብቁ እንዳይሆን ያደርጋል። MYPAmh 178.5

እግዚአብሔር ለአብዛኞቹ ወጣቶቻችን ታላላቅ ችሎታዎችን ሰጥቷቸዋል! ነገር ግን ብዙ ጊዜ ኃይሎቻቸውን አዳክመዋል፣ አእምሮኣቸውን ግራ በማጋባት አዳክመውታል። ጥበብ በጎደለው የንባብ ምርጫቸው ምክንያት ለአመታት ስለ እምነታችን ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ በፀጋም ሆነ በእውቀት አላደጉም። የጌታን ቶሎ መምጣት የሚጠባበቁና “ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ” ያለውን አስደናቂ ለውጥ የሚጠብቁ በዚህ የምህረት ጊዜ ውስጥ ከፍ ያለ ተግባር ሊፈፅሙ በሚችሉበት ቦታ መቆም አለባቸው። MYPAmh 178.6

ውድ ወጣት ወዶጆቼ ሆይ፣ ስሜትን የሚያነሳሱ ታሪኮችን ተፅእኖ በተመለከተ የራሳችሁን ልምምድ ጠይቁ። እንደዚህ ዓይነት ንባብ ካነበባችሁ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ከፍታችሁ የሕይወትን ቃላት በፍላጎት ማንበብ ትችላላችሁን? የዚያ የፍቅር ታሪክ ውበት በአእምሮችሁ ስላለ ጤናማ የአእምሮን አስተሳሰብ በማበላሸት ዘላላማዊው ደህንነታቸሁን በተመለከተ የተገለፁ ጠቃሚና ታላላቅ እውነቶች ላይ ትኩረታችሁን እንዳታደርጉ ያደርጋል። MYPAmh 179.1

ጠቃሚነት የሌለውን ርካሽ ንባብ በሙሉ በፅናት አስወግዱት። መንፈሳዊነታችሁን አያጠነክርላችሁም፣ ነገር ግን በአእምሮአችሁ ውስጥ አስተሳሰብን የሚያዛቡ ስሜቶችን በማስገባት ስለ ኢየሱስ ጥቂት እንድታነቡና በእርሱ ትምህርቶችም ላይ የምታሳልፉት ጊዜ አነስተኛ እንዲሆን ያደረጋል። አእምሮአችሁን በተሳሳተ አቅጣጫ ከሚመራ ከማንኛውም ነገር ራሳችሁን ጠብቁ። አእምሮአችሁን ለጥንካሬው ምንም አስተዋፅኦ በማያደርጉ ርካሽ ታሪኮች አታጨናንቁት። አስተሳሰቦቻችን ለአእምሮዎችን ከሰጠነው ምግብ ጋር ተመሳሳይ ባህሪይ አላቸው። MYPAmh 179.2