መልዕክት ለወጣቶች
አእምሮ ክፍት መሆን
በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችሁ ከዚህ በፊት በአእምሮአችሁ ይዛችሁት የነበረውን ግምትም ሆነ በውርስና በሂደት ያዳበራችሁትን አሳብ በምርምር በር ላይ አስቀምጡት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችሁ አሳብ ድጋፍ እንዲሆን የምታጠኑ ከሆነ በፍጹም እውነትን ማግኘት አትችሉም፡፡ እነዚህን አሳቦች በበር ላይ ተውና ዝቅ ባለ ልብ ጌታ የሚላችሁን ለመስማት ሂዱ፡፡ ትሁት የሆነ የእውነት ፈላጊ በክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ከእርሱ ሲማር ቃሉ ማስተዋልን ይሰጠዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት በራሳቸው ማስተዋል እጅግ ጠቢባን ለሆኑ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡- ለደህንነት ጠቢባን መሆን ከፈለጋችሁ በልባችሁ ትሁታንና የዋሃን ሁኑ፡፡ MYPAmh 170.5
ቃሉን ከዚህ በፊት በነበራችሁ አስተሳሰብ አታንብቡ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ከመወሰን ነፃ በሆነ አእምሮ በጥንቃቄ በጸሎት መርምሩ፡፡ ስታነቡ ሳለ ለአእምሮአችሁ የሚያሳምን አሳብ ከመጣላችሁና ከዚህ በፊት ይዛችሁ የኖራችሁት አሳብ ከቃሉ ጋር የማይስማማ ከሆነ ቃሉ ከእናንተ አሳብ ጋር እንዲገጥም ለማድረግ አትሞክሩ፡፡ እናንተ የነበራችሁ አስተሳሰብ ከቃሉ ጋር ገጣሚ እንዲሆን አድርጉ፡፡ ከዚህ በፊት የምታምኑትም ሆነ ስትለማመዱት የኖራችሁት ነገር ማስተዋላችሁን እንዲቆጣጠር አትፍቀዱ፡፡ ከሕጉ ተዓምራትን ለማየት የአእምሮ ዓይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡ የተጻፈው ምን እንደሆነ አግኙና እግራችሁን በዘላለማዊው ዓለት ላይ አቁሙ፡፡ MYPAmh 170.6