መልዕክት ለወጣቶች
መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት የማይደክም
ጥረት #መጽሐፍትን እሹ፤ በእነርሱ የዘላለም ሕይወት የምታገኙ ይመስላችኋልና፣ እነርሱ ግን ስለ እኔ የሚናገሩ ናቸው፡፡” መሻት ማለት የጠፋ ነገርን ለማግኘት ተግቶ መፈለግ ማለት ነው፡፡ የተደበቁ ሃብቶችን ለማግኘት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ፈልጉ፡፡ እነዚህ ሳይኖሩአችሁ መኖር አትችሉም፡፡ ከባድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን አንዱን ከሌላኛው ጋር በማነፃፀር አጥኑ፡፡ ያኔ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን የሚከፍት ቁልፍ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡ MYPAmh 170.1
መጽሐፍ ቅዱስን በጸሎት የሚያጠኑ ከእያንዳንዱ ጥናታቸው በኋላ ከመጀመሪያ የበለጠ ጠቢባን ይሆናሉ፡፡ አንዳንድ ችግሮቻቸው ይቃለሉላቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አሥራ አራት ላይ የተገለጸውን አድርጎላቸዋል፡፡ «አባቴ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ ያስታውሳችኋል፡፡» MYPAmh 170.2
ያለ ልባዊና የማይደክም ጥረት ልናገኘው የሚገባውን ጠቀሜታ ያለውን ማንኛውንም ነገር አናገኝም፡፡ በንግድ መስመር አንድን ነገር ለማድረግ ፈቃደኝነት ያላቸው ብቻ የተሳካ ውጤት ያገኛሉ፡፡ ያለ ልባዊ ጥረት የመንፈሳዊ ነገሮችን እውቀት ለማግኘት መጠበቅ አንችልም፡፡ የእውነትን እንቁዎች ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች አንድ ማዕድን ቆፋሪ ውድ የሆኑ የከበሩ የማዕድን ክምችቶችን ለማግኘት እንደሚቆፍር ሁሉ እነርሱም መቆፈር አለባቸው፡፡ MYPAmh 170.3
በግድ የለሽነትና በሁለት ልብ የሚሠሩ ሰዎች ክንውንነትን አያገኙም፡፡ ወጣቶችና አዛውንት ቃሉን ማንበብ አለባቸው፡፡ ማንበብ ብቻም ሳይሆን በትጋት፣ ከልባቸው በመጸለይ፣ በማመንና በመሻት ማጥናት አለባቸው፡፡ ያኔ ጌታ ማስተዋላቸውን ስለሚያነሳሳ የተሰወራውን ሃብት ያገኛሉ፡፡ MYPAmh 170.4