መልዕክት ለወጣቶች

281/511

የክርስቶስ የማማለድ ሥራ

የእግዚአብሔር ውድ ልጅ በራሱ መለኮታዊ ሰውነት ፍጡሩን ከፈጣሪ፣ ውስን ሰውን ከዘላለማዊው ጋር ለማገናኘት የሚሠራው ሥራ አስተሳሰባችንን ለሕይወት ዘመን በሙሉ መያዝ የሚችል ትምህርት ነው፡፡ ይህ የክርስቶስ ሥራ በሌሎች ዓላማት ላሉት ፍጡራን ለየዋህነታቸውና ታዛዥነታቸው ማረጋገጫ ለመስጠትና በዚህ ዓለም የጠፉትንና ወደ ሞት እየሄዱ ያሉትን ለማዳን ነው፡፡ አመፀኞች ወደ አምላካቸው መመለስ የሚችሉበትን መንገድ የከፈተ ሲሆን በዚያው ተግባሩ በንጽህና ያሉት እንዳይረክሱ በዙሪያቸው ጥበቃ ለማድረግም ጭምር ነው፡፡ MYPAmh 166.3

ወደ ኃጢአት በፍጹም ያልወደቁ ዓላማት በመኖራቸው ደስ እያለን እነዚህ ዓላማት ለወደቁት የአዳም ልጆች ስለተዘጋጀው የደህንነት እቅድና ራሳቸውን ባላቸው የባሕርይ ንጽህና ቦታ ለማጽናት ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጋና፣ አክብሮትና ሙገሳ ያቀርባሉ፡፡ ሰይጣን በፈተናው አማካይነት በሰብዓዊ ዘር ላይ ያመጣውን ጥፋት ያነሳው እጅ በሌሎች ዓላማት ያሉትን ፍጥረታት ከኃጢአት የጠበቀ እጅም ነው፡፡ እያንዳንዱ ዓለም በአጠቃላይ የሚኖረው በአብና በወልድ ጥንቃቄና ድጋፍ ነው፡፡ ይህ ጥንቃቄ በኃጢአት ለወደቀው ቤተሰብ ሁልጊዜ የተደረገ ነው፡፡ ክርስቶስ ለሰው እያማለደ ነው፤ የማይታዩ ዓላማት ሥርዓትም በእርሱ የማማለድ ሥራ ተጠብቋል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ሐሳቦቻችንን ለመያዝና እግዚአብሔርን እንድናመሰግንና እንድናመልክ ለማድረግ በቂ መጠንና ጠቀሜታ የላቸውምን? MYPAmh 166.4