መልዕክት ለወጣቶች

280/511

መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ዋጋ

የአእምሮ ችሎታን ለማጠንከር ከማንኛውም ጥናት ይልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይበልጣል፡፡ ወጣቶች በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለመመርመር ምንኛ ሰፊ የሆኑ የጥናት መስኮችን ያገኙ ይሁን! አእምሮ እውነትን ለማስተዋል በሚያደርገው በእያንዳንዱ ጥናት በምርምሩ ውስጥ እየጠለቀ ይሄዳል፡፡ ሆኖም መጨረሻ የሌለው እውቀት ባሻገር አለ፡፡ MYPAmh 166.1

እግዚአብሔርን እንደሚወዱና ለተቀደሰ ነገር አክብሮት እንዳላቸው እየተናገሩ ግን አእምሮአቸው ጥልቀት ወደ ሌላቸውና እርግጠኛ ወዳልሆኑ ነገሮች እንዲወርድ የሚፈቅዱ ሰዎች ራሳቸውን በሰይጣን ቁጥጥር ሥር እያደርጉና የእርሱን ሥራ እየሰሩ ናቸው፡፡ ወጣቶች በተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን የእግዚአብሔርን ባለ ግርማ ሥራዎችና በቃሉ ውስጥ እንደተገለጸ ግርውንና ኃይሉን ቢያጠኑ ኖሮ ከእያንዳንዱ ተግባር ውስጥ ኃይላቸው ተነቃቅቶና ከብሮ ይወጣሉ፡፡ ለትዕቢት ምንም ቦታ ሳይሰጥ ብርታት ይገኛል፡፡ አእምሮ የመለኮታዊ ኃይል ድንቆችን በማሰላሰል ሰብዓዊ ጥበብ ከዘላለማዊው ጋር ካልተገናኘና በክርስቶስ ፀጋ ካልተቀደሰ በቀር ሞኝነት መሆኑን የሚገልጸውን ከባድ ግን እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ትምህርት ይማራል፡፡ MYPAmh 166.2