የወንጌል አገልጋዮች
ለነፍሳት የሕይወት አንጀራን መቁረስ
ወንጌላዊያኖቻችን ከሚያስተምሯቸው ሕዝቦች አብዛኛዎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸው ያልበሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉ ትምህርት አንደ አዲስ ሆኖ ይታያቸዋል፡፡ እነዚህን ሰዎች ከዕውነት ጋር ሲያስተዋውቅ ወንጌላዊው የማወቅ በማነሳሳት ዘዴ ማስተማር አለበት፡፡ ለእነዚህ ለተራቡ ነፍሳት የሕይወት አንጀራን ይቁረስላቸወ፡፡ ለመዳን ምን ማድረግ አንደሚገባቸው የማይገልጽ ትምህርት ማቅረብ ፈጽሞ አይገባውም፡፡ GWAmh 94.4
የእነዚህ ሰዎች አስቸኳይ ፍላጐቶችና ችግሮች ፈጣን መፍትሄ ማግኘት አለባቸው፡፡ ወንጌላዊው የጣፈጠና የተሳካ ቋንቋ በመጠቀምና ቅኔ ነክ አነጋገር በማንቆርቆር የሰዎችን ስሜት ያረካ ይሆናል፡፡ ግን ይህ ዓይነት ትምህርት ለዘለዓለማዊ ዕድገታቸው የሚሰጠው ጥቅም የተወሰነ ነው፡፡ በጣፈጠ አነጋገሩ ነፍሳቱን ያረካ ይመስለው ይሆናል፡፡ ሰዎችም ከአሁን ቀደም ቃለ-እግዚአብሔር በቋንቋ ውበት እንደዚህ አጊጦ ሰምተን አናውቅም ይሉ ይሆናል፡፡ GWAmh 94.5
እንደዚህ ያለ በቋንቋ አበባ አጊጦ የተሰጠ ትምህርት በውስጡ ቁም ነገር ቢገኝበትም አዳማጮቹን ለታላቁ ጦርነት አያዘጋጃቸውም፡፡ የአነጋገርን ጣዕም ዋና ዓላማ አድርጎ የሚሰለፍ ወንጌላዊ የተናገረውን ቃል አዳማጮቹ እንዲረሱ ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ የአዳማጩ የስሜት እንቅስቃሴ ሲበርድ የእግዚአብሔር ቃል ከአእምሮው ይፋቃል፡፡ ምንም ነገር እንዳላስተዋለ ይሰማዋል፡፡ የተናጋሪውን የንግግር ችሎታ በአድናቆት ይናገር ይሆናል፤ ግን ወደ እግዚአብሔር አንድ አርምጃም አልቀረበም፡፡ አገልግሉቱን አንደ ቲያተር ወንጌላዊውን እንደ ተዋናይ ይመለከተዋል፡፡ ደጋግመጡ ቢያዳምጡትም ልባቸው ከቶ አይነካበትም፣ አይመገቡምም፡፡ GWAmh 95.1
ደስ የሚያሰኙ ዓረፍተ ነገሮች ወይም ትርጉም የሌላቸው ሐረጐች ተፈላጊነታቸው አምብዛም ነው: ወንጌላዊያን ሰሚዎች የተጨበጠ እውነት ማስያዝ አለባቸው፡፡ ወዳጆቼ ሆይ፣ ተራው ሕዝብ በማያስተውላችሁ ዘዴ አትድከሙ ወይም ቢያስተውሉትም በረከት በማያገኙበት መንገድ መቸገር የለባቸውም፡፡ በክርስቶስ የተገለጠውን ቀላልና ቀጥተኛ ትምህርት አስተምሩ፡፡ የክርስቶስን ራስን የመካድና የመሥዋዕትነት ሕይወት፣ ሕይወትና ሞቱን፣ ትንሣኤውንና ዕርገቱን፤፣ በሰማይ ቤተመቅደስ ለኃጢዓተኞች አማላጅነቱን አስተምሩ፡፡ በየጉባዔው የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያንዣብብባቸው- ሰዎች : እውነቱን አንዲለዩ ዕርዷቸው:: የሕይወት እንጀራን ቁረሱላቸው፡፡ በአእምሮአቸው ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ጥያቄዎች ልታሳድሩባቸው ይገባል፡፡ GWAmh 95.2
ብዙ ሰዎች ሀሰትን ያስተምራሉ፣ እናንት ግን ስለ እውነት በእውነት ተሟገቱ። ለእግዚአብሔር በጐች አንደ ለመለመ መስክ የሚቀጠፍ የነፍስ ምግብ አቅርቡላቸው፡፡ GWAmh 95.3
ሳታስተምሯአቸው በፊት ወደ ሕይወት ምንጭ ከቀረቡበት ቦታ አርቆ በሚወስድ የተሳሳተ መንገድ አትምሯአቸው። የሱስ እንዳደረገው ሁሉ የኦሪትንና የወንጌልን ቀዳሚነት አስተምሩ፡፡ ክርስቶስ እውነት፣ መንገድ፤ ሕይወት መሆኑን ማስተማር አለባችሁ:: ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ለማዳን መቻሉን ማሳወቅ ተግባራችሁ ነው፡፡ የጦር አለቃችን ክርስቶስ በአባቱ ፊት ለሕዝቡ ቢያማልድም በማግባባት ሳይሆን በድል አድራጊነት ደረጃ መሆኑን አስረዱ፡፡ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ: እውነቱን ቁልጭ ባለ በማያጠራጥር መምህርነት አቅርቡ፡፡ GWAmh 95.4
ወንጌላዊያን ካልተጠነቀቁ በቀር የእግዚአብሔር ቃል እውነት በሰብዓዊነት ወስጥ ደብቀው ያስቀሩታል። ማንም ወንጌላዊ በቃሉ ማማር ነፍስ አመልሳለሁ ብሎ አይነሳ፡፡ ሌሎችን የሚያስተምር ሰው መንፈስ ያድለው ከንድ እግዚአብሔርን ይለምን፡፡ ክርስቶስ የኃጥዓን ሁሉ ተስፋ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ይህን ተስፋ የሚሰሙ ሰዎች በጆሮአቸው እንደ ጣፋጭ ዜማ ይሆንላቸዋል፡፡ ኃጢዓተኛው ሊሰማው የሚገባው ተስፋ «እግዚአብሔር እንዲሁ ዓለሙን ወዷልና አንድ ልጁን እስኪለውጥ ድረስ በእርሱ ያመነ ሁለ አንዳይጠፋ የዘለዓለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጅ” የሚለውን ነው፡፡ (ዮሐንስ 3:16): GWAmh 96.1
ወንጌልን ለመቀበል ጥልቅ ትምህርት ረዥም ክርክር ወይም የንግግር ማማር አያስፈልግም፡፡ ግን የወንጌልን እውነትና የሕይወትን እንጀራ፣ የተራበ ነፍስ ሊቀበለው ይችላል፡፡ GWAmh 96.2
የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የወንጌልን ሥራ እርምጃ ያፋጥነዋል፡፡ ወንጌላዊው የእግዚአብሔርን ቃል ሲያቀብል መንፈስ ትዱስ የሰሚዎቹን ልብ አንዲቀበል ያዘጋጀዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የማይገታ ኃይል ነው አንጂ አገልጋይ አይደለም፡፡ ቃሉ እግዚአብሔር በሰዎች አፅምሮ ውስጥ አንዲበቅልና አገልጋዩ በጥበብ ቃሉን አንዲዘራ ይረዳዋል፡፡ ነፍስን በቅድስና የሚጠብቅ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በኃጢዓት የሚዋኙትን አንዳይሰጥሙ ያስጠነቅቃል፡፡ በሞተ መንገድ የሚጓዙትን መክሮ ይመልሳል፡፡ GWAmh 96.3