የወንጌል አገልጋዮች

64/217

አንደ ሹል ቀስቶች

የክርስቶስ ቃል የተፈለገውን ቦታ የሚወጋና እንደሹል ቀስት ሰርስሮ የሚገባ ነው:: አዳማጮቹ ቢበዙም ቢያንሱም ቃሉ በአንዳንድ ሰዎች የማዳን ኃይል ሳይፈጽም ቀርቶ አያውቅም፡፡ ከከንፈሩ የወጣ መልዕክት ያለ ውጤት ቀርቶ አያውቅም፡፡ የተናገረው ቃል ሁሉ በሰሚዎቹ ላይ ሽክም ይጥልባቸው ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን በክርስቶስ ኃይል እየተረዱ መልዕክቱን የሚያዳርሱ መልዕክተኞች ድካማችን ያለዋጋ በክንቱ ይቀራል ብለው መሥጋት የለባቸውም፡፡ የዕውነት ቀስት ሲወረወር ለሰብዓዊ ዓይን ባይከሰትም አንኳ ዓላማውን ስቷል ማለት አይቻልም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል የቆሰለውን ሰው ድምፅ ሰብዓዊ ጆሮ ሊያዳምጠው ባይችልም የእግዚአብሔር ቃል አይፈታም፡፡ GWAmh 93.1

እግዚአብሔር ለሰዎች ልብ ይናገራል፡፡ በመጨረሻ ቀን ታማኝ አገልጋዮቹ የድል ክብር ተካፋይ ሆነው ይገኛሉ:: በመንፈስ ቅዱስ ሳይነሳሱ ወንጌልን አስተምራለሁ ብሎ መሰለፍ ለራስ የጥፋትን ጉድጓድ እንደመማስ ከመቀጠሩ በላይ ለሌሎችም እንቅፋት መሆን ነው:: በእየጉባዔው ሕይወታቸውን ለጌታ ለማስረከብ ቁርጥ ውሳኔ ያላደረጉ ፈራ ተባ የሚሉ ነፍሳት አሉ:: ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ እነዚህን የሚያመነቱ ነፍሳት አንዲወስኑ ለመርዳት ወንጌላዊው ኃይል ያንሰዋል፡፡ GWAmh 93.2

በዚህ የግብረ-ገብ ጨለማ በሰፈነበት ዘመን ነፍሳትን ለመመለስ ደረቅ ዕውቀት ብቻ አይበቃም፡፡ ወንጌላዊያን ከአግዚአብሐር ጋር የማያቋረጥ ግንኙነት መመሥረት አለባቸው:: የሚናገሩትን አምነውበት ማስተማር አለባቸው፡፡ ከእውነተኛ የእግዚአብሔር ሰው ከናፍር የሚወጡ ቅዱስ ቃላት ኃጢዓተኛውን ያስረዳሉ፣፤ (ያንቀጠቀጣሉ)፡፡- ስህተቱን የተገነዘበውን ከአምላኬ ጐን ለመቆም ቆርጫለሁ ያሰኛሉ፡፡ የአምላክ ሠራተኛ የበለጠ ብርሃንና ኃይል ለመቀበል ከመጣር ከቶ ሊቆጠብ አይገባውም፡፡ በርትቶ መሥራት፣፤ መጸለይ፤ ተስፋ ሲቆርጥና ሲቸገር፣ ጨለማም ዙሪያውን ሲከበው አግዚአብሐርን በበሰጠ ለመረዳት መሞከር የዕለት ተግባሩ ይሁን፡፡ አንድን ነፍስ አንኳን ለመመለስ ያለፍርሃት በድፍረት ፊት መገሥገሥ አለበት፡፡ GWAmh 93.3

ክርስቶስ «አልተውህም፣ አልረሳህምም” ብሏልና፣ የጽድቅን አክሊል ለመቀዳጀት ወንጌላዊያን ክርስቶስ የጣለባቸውን አደራ ማክበር አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ከአምላክ ተቀብለው ለሰዎች የሚያስተላልፉ ሰዎች ምሣሌነታቸው ሰዎችን ሊጐዳም ሊጠቅምም መቻሉ በራሳቸው ኃላፊነት የተወሰነ መሆኑን ይገነዘባሉ፡፡ ዕውነተኛ የእግዚአብሔር ሰዎች ከሆኑ ወንጌልን የማስተማር ዓላማ የሰዎችን ስሜት ለማስደሰት አለመሆኑ ይገባቸዋል፡፡ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ወይም አስተሳሰብን ለማጐልመስ ብቻ አይደለም፡፡ GWAmh 94.1

እርግጥ ቃለ-አግዚአብሐር ለሰዎች የአእምሮ ብስለትን መስጠት አለበት:: ግን ዋናው ዓላማው ይህ አይደለም፡፡ ቃለ-እግዚአብሔር የአዳማጩን ልብ ጠልቆ መንካት አለበት፡፡ ወንጌላዊው ሲያስተምር ጣፋጭ ታሪኮችን መደርደር አያስፈልገውም፡፡ ለሰዎች የሚጠቅመውንና የሚያስፈልገውን ዘለዓለማዊ እውነት ተጠንቅቆ ማስረዳት አለበት:: GWAmh 94.2

በጉባዔው ፊት ሲቆም ከአዳማጮቹ መካከል በጥርጥር ውሽንፍር የሚንገላቱ፤ ተስፋ የቆረጡ፣ ለወደፊት አለኝታ በልባቸው ያላደረባቸው፤ ፈተና ሁልጊዜ የሚያንገላታቸው፣፤ ከጠላት ጋር የማያቋርጥ ትግልና ጦርነት በማካሄድ ላይ ያሉ ነፍሳት መኖራቸውን ኣይዘንጋ፡፡ ከጠላት ጋር በሚያደርጉት መውጊያ ብርታት የሚሰጧቸው ቃላት መናገር ያስችለው ዘንድ አምላክን ይለምን፡፡ GWAmh 94.3