የወንጌል አገልጋዮች

2/217

ምዕራፍ 1—ቅዱስ ጥሪ

ሀ - በክርስቶስ ምትክ

በየትኛውም ክፍለ ዘመን ቢሆን ክርስቶስ «ምስክሮቼ» ብሎ የሚጠራቸው የታደሉ ሰዎች በምድር ላይ አልታጡም፡፡ በዘመኑ ሁሉ ብርሃናቸውን ለሰዎች ያበሩ፣ ቃለ-እግዚአብሔርን ለሌሎች ሰዎች ያካፈሉ ቁም ነገረኞች ሰዎች በዓለም ላይ ነበሩ፡፡ ሄኖክ፤ኖህ፤ሙሴ፤ ዳንኤልና ሴሎችም ብዙ አበውና ነብያት «የጽድቅ አገልጋዮች» የሚል ስያሜ አግኝተዋል፡፡ ስጋ የለበሱ ስለነበሩ ደካሞችና ተላላዎች ነበሩ፣ ነገር ግን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስሳስረከቡ መሣሪያዎቹ አደረጋቸው፡፡ GWAmh 8.1

ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ በወኪሎቹ አማካይነት ሥራውን ያካሄዳል፡፡ በክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ለመሥራት መመረጥ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበት የሥራ ደረጃ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ኃላፊነት የወደቀባቸው ሰዎች ሰዎችን ከአምላክ ጋር ለማስታረቅ የሚጥሩ ናቸው፤ ይህን ታላቅ ሥራም ከላይ ጥበብና ኃይል ካልተቀበሉ ሊፈጽሙት አይችሉም፡፡ GWAmh 8.2

የእግዚአብሔር አገልጋዮች መጀመሪያውም መደምደሚያውም ራሱ ሆኖ በሚጠብቃቸው ሰባት ክዋክብት ይመሰላሉ፡፡ የቤተ-ክርስቲያን አራአያነት የሚገለጠው የክርስቶስን ፍቅር በሚያስተዋውቁት አገልጋዮቹ ነው:: የሰማይ ክዋክብት በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡ ብርሃንን አድሎ አንቅስቃሴአቸውን ሁሉ የሚቆጣጠር እርሱ ነው:: አገልጋዮቹም እንደዚሁ ከእርሱ ብርሃንን ተቀብለው ለሌሎች ያበራሉ፡፡ ከከዋክብት ድምቀት ይልቅ አገልጋዮቹ መልዕክቱን ለሌሎች ሲያስተላልፉ ደስታና ክብር ለእግዚአብሔር ይሰጠዋል፡፡ በእርሱ ሲታመኑበት ብርፃኑን ለሌሎች እንዲያበሩ ያድላቸዋል፡፡ GWAmh 8.3