የወንጌል አገልጋዮች
የወንጌል አገልጋዮች
መግቢያ
በዚህ መጽሐፍ ጽንሰ ሃሳብ፣ ቅርጽና ድባብ ዙሪያ ጥቁት ዐረፍተ ነገሮች ደርድሮ “መግቢያ’ በሚል ርዕስ የእንባቢውን ትኩረት በመሳብ ፋንታ የተደራሲወ የትኩረት አቅጣጫ በመጽሐፉ “ማውጫ” ላይ ቢሆን የተሻለ ተገቢነት እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ በመሆኑም እንባቢወ‹ በመጽሐፉ ማውጫ ቁልቁል ወደ ተደረደሩት ርፅሰ ጉዳዮች ካማተረ፤ አእምሮው መምሪያ አዘል ወደሆኑት በአጅጉ አንገብጋቢ ጽንሰ ሀሳቦችና መጠነ ሰፊ ተጨባጭ እውነቶች በመቀላሉ መሳቡ እሙን ነው፡፡ GWAmh 6.1
1. የወንጌል አገልጋዩና ፈቃደኛው ወንጌላዊ በዚህ መጽሐፍ በተለይ ቢጠቀሱም መልእክቱ በአጠቃላይ ለወንጌል ሠራተኛው ጉልህ ጠቀሜታ ያለው ለመሆኑ ሥራው ስንቶችን ሊያቅፍ ይገባል? የወንጌል በረከት ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ይህ የምስራች የሚያስገኘውን ጥቅም ለሌሎች ይፋ የማድረግ ሥራ የመሥራት ጥረት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ስለዚህ የዚህ ሥራ መመሪያ ጠቀሜታ ሁሉንም ወገኖች ያማከለ ነው፡፡ GWAmh 6.2
2. በመጽሐፉ የሚስተዋሉት መመሪያዎች በሙከራ መልክ የቀረቡ ሳይሆን በሚገባ የተፈተሹና ተፈትሸው የተረጋገጡ መርኅች ናቸው፡፡ ብዙዎች በመጽሐፉ በቀረቡት እውነቶች ላይ ጥናት አድርገዋል፣ ለመመሪያ አዘሎቹ ቃላት ጆሮዎቻቸውን ሰጥተዋል አንዲሁም የቀረቡትን ምክረ ሃሳቦች ለመከተል ሞከረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የተገኙት ውጤቶች ሁሌም አስደሳች ከመሆናቸው ባሻገር ፍሬያቸውም አመርቂ ሆኖአል፡፡ እነዚህ ወገኖች መልእክቱን ለራሳቸው በጥልቅ መመልከትን ጨምሮ ለሌሎችም ጉልህ ጠቀሜታ አንደሚኖረው በማመናቸው መጽሐፉ አሁን በያዘው ቅርጽና ይዘት ሰእንባቢ አንዲቀርብ አንዱ ምክንያት ሆኗል፡፡ GWAmh 6.3
መጽሐፉ የታቀደው ዓይነት መጠን አንዲኖረው መፈለጉን ተከትሎ “ቴስቲሞኒስ” በመባል ከሚታወቀው ሥራ የተወሰኑ ከፍሎችን ማስቀረት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመጽሐፉ ሳይካተቱ የቀሩ ሃሳቦች የነጠብጣብ ምልከት የተደረገባቸው ሲሆን፤ ከ“ቴስቲሞኒስ” መጽሐፍ የተወሰዱ ሃሳቦች በትምህርት ጥቅስ አንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ከኤለን ጂ. ኋይት የታተሙም ሆኑ ያልታተሙ ሥራዎች የተወሰዱ ጽሑፎች ስለጸሐፊዋ ተገቢው አጽንኦት ተሰጥቶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ GWAmh 7.1
3. እንባቢው እያንዳንዱን የዚህን መጽሐፍ ገጽ በቅን ልቦናና በትጋት በማጥናት በመልእከቱ የቀረቡትን መመሪያዎች ይተገብር ዘንድ የአሳታሚዎቹ አደራ ነው፡፡ ይህ ሥራ ጌታ በምድር ላለው ዓላማ ዘላቂና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በማምጣት የአምላካዊው በረከት ምንጭ ይሆን ዘንድ የአሳታሚዎቹ አምነት ነው፡፡ GWAmh 7.2
አሳታሚዎቹ