የወንጌል አገልጋዮች

18/217

ክርስቶስ መምህር

የዓለም አዳኝ መልካም በማድረግ ኖረ፡፡ የሕይወትን ቃል በትህትና ሲያስተምር የአዳማጮቹን ገጽ ሲመለከት በናፍቆትና በደስታ የሚያዳምጡትን ሰዎች ፊት ሲመለከት ለልቡ ደስታ ይሰማው ነበር፡፡ ኃጢዓቱና ስህተቱ በእግዚአብሔር ቃል ሲነሳበት ፊቱን የሚያጨፈግገውንና የማዳንን ዕድል ችላ ያለውን ሰው በፊቱ ያውቀው ነበር፡፡ አዳማጮቹ የሚያስፈልጋቸው ኃጢዓትን መጥላት መሆኑን የሱስ እንደሚያውቅ ቢቀበሉት ኖሮ በጨለማው አእምሮአቸው የበራው ቃለ-እግዚአብሔር በጠቀማቸው ነበር፡፡ GWAmh 29.1

ክርስቶስ ሰማስተዋወቅ የፈለገው ዕውነትን ለተከተላት ለነፍስ ደስታና ሰላምን መስጠቷን ነበር፡-፡ ጠለቅ አድርጐ በመመልክት ሳይገለጥ ሰውን ከአምላክ የሚለየውን የተደበቀ ኃጢዓት ሊያይ ኃጢዓቱን በማመላከት ከሰውየው እንዲወገድ ለማድረግ ይጥራል፡፡ ለአንዳንዶቹ ለቀረቡት የመዳን ተስፋ አሳደረባቸው፡፡ ዕውነተኛ ተከታዮቹ አደረጋቸው፡፡ GWAmh 29.2

የቃሉ ቀስት ወደልባቸው ገብቶ የራስን መውደድ መጋረጃ አስወግዶ ትህትናን ሲያጐናጽፋቸው የክርስቶስ ልብ በደስታና በተድላ ይሞላል፡፡ በዓይኑ ጉባዔውን ሲቃኘው ክርስቶስ ብዙዎቹ የመንግሥቱ አንደሚሆኑ ተስፋ አደረገ፡፡ GWAmh 29.3

በእርሱ ፈንታ የሚልካቸው የክርስቶስ መልዕክትኞችም የዚሁ ዓይነት ስሜት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሥራቸው ተቀባይነት ያላገኘ መስሏቸው ተስፋ ወደመቁረጡ የተቃረቡ ቢኖሩ ክርስቶስ ከእነርሱው የባሰ ተቃውሞ ገጥሞት አንደነበር ማስታወሱ ይጠቅማቸዋል፡፡ ሕዝቡን በትዕግሥት በፍቅር አስተማረ፡፡ ጥልቅ በሆነው ጥበቡ የእያንዳንዱን ሰው ፍላጐት ተንገነዘበ:: መልዕክቱን ከመቀበል አሻፈረን የሚሉትን ሲመለከት ለጠፉት ነፍሳት ከልቡ ያዝን ነበር:: የመድህናችን ትምህርት የታይታ አልነበረም፡፡ ሰዎች በሥጋዊ ዓይናቸው የአምላክን ልጅ ክብር ሊመሰከቱት አልቻሉም፡፡ GWAmh 29.4

«በፊቱ፤ አንደቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት አንደሣር አድርጐአል፤ መልክና ውበት የለውም የተናቀ ከሰውም የተጠላ የሕማም ሰው ደዌን የሚያውቅ ነው፡፡ ሰው ፊቱን አንደሚሠውርበት የተናቀ ነው፤ እኛም አላከበርነውም፡፡» «የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራች አስብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እፈውስ ዘንድ፣ለተማረኩ ነፃነት ለታሠሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ክርስቶስ ሰዎችን ባሉበት ደረጃ ያገናኛቸው ነበር፡፡ ግልጽ የሆነ ዕውነት በሚማርክ ቀላል አነጋገር ያቀርብላቸው ነበር፡፡ በጣም ጥልቅ የሆነውን የዕውነት ምስጢር ያልተማሩት መሀይማን ሊያስተውሉት ይችላሉ፡፡ ምን ማለቱ ይሆን ብሎ ማንም ለመረዳት አዋቂ መጠየቅ አላስፈለገውም፡፡ መሃይማንን ለማደናገር ከባድ ትርጉም ያዘለ ቃል አይናገርም: ከአለም መምህራን ሁሉ የላቀውና የታወቀው መምህር የማስተማር ዘዴው በጣም ቀላልና የሚስተዋል ነበር፡፡ GWAmh 30.1

«ለሰው ሁሉ የሚያበራው ዕውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር:: ቃልም ሥ'ጋ (ፀጋንና ዕውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ፡፡ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳሰው የሆነውን ክብሩን አየን፡፡ መቸም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድም ሰው የለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው፡፡» GWAmh 30.2

መምህራንን ሁሉ ብንዘረዝር የክርስቶስ ብርሃን ነበረባቸው፡፡ ጨረቃ የፀሐይን ብርሃን አንደምታንፀባርቅ መምህራን ሁሉ ዕውነተኛ ከሆኑ የጽድቅን ፀሐይ ያንፀባርቃሉ፡፡ እያንዳንዱ የማሰብ ችሎታና ፍልስፍና ዕውነተኛ ከሆነ ከዓለም ብርሃን ያፈለቀ ነው:: ኢሣይያስ 53፡፡2:3፤ ኢሣይያስ 61:17 ዮሐንስ 1:9:14:18:: GWAmh 30.3