የወንጌል አገልጋዮች

17/217

ለሀብታምና ለደኻ አኩል

ኑሮው ይሰራ ነበር፡፡ ልባቸው ያዘነባቸውን ሲያጽናና የደከሙትን ሲያበረታታ ይውላል፡፡ ባለፀጋ፣ ልበ-ቅን፣ መምህር ሁሉንም ያበረታታ ነበር፡፡ ድሆችን ሲያገለግል ባለፀጐችንም እንዴት እንደሚያስተምር ዘዴ ከመሻት አልቦዘነም፡፡ ሀብታሞችን፣ ባለፀጐች፤- ታላላቆችን አይሁዶች፤ የሮማዊያን ገዥዎች ተዋወቃቸው፡ ግብዣቸውን ተቀበለ፡፡ ዓመት በዓላቸውን አከበረ፡፡ ስለሥራቸውና ስለኑሮአቸው በዝርዝር አወቀ፡፡ GWAmh 27.4

ክርስቶስ ለሰዎች ከላይ ኃይል በመቀበል ንጹህ ሕይዎት ለመኖር መቻልን ገለጸላቸው፡፡ በትዕግሥትና ባለመሰልቸት የተፈለገውን ዕርዳታ አሟላላቸው፡፡ በምህረት አጁ የነካቸው ሁሉ ለነፍሳቸው ዕረፍትን ተቀብለው፣ ጠላትነትን ወደ ፍቅር፣ አለማመንን ወደ ዕምነት ለወጡ፡፡ GWAmh 28.1

ክርስቶስ የወገንና የደረጃ ልዩነት አላደረገም፡፡ ጸሐፍትና ፈሪሣዊያን የወገን ልዩነት በማድረግ ከወገናቸው ውጭ የሆኑትን ከሰማይ ቤት ሊያስቀሩ ተመኙ፡፡ ክርስቶስ ግን የመለያየትን ገደብ ለማፈራረስ መጣ፡፡ ምህረቱ ምድርን ሁሉ አንደሚያዳርሱት አንደ አየር፣እንደብርሃንና እንደ ዝናብ ጠል ለሁሉ መሆኑን አሳየ:: የክርስቶስ ሕይወት አሕዛብና አይሁድ፣ ባሪያና ጌታ፣ የሚባል ነገር ሳይኖር ሁሉም ወንድማማች የሚሆንበት ሃይማኖት መሠረተ፡፡ GWAmh 28.2

ደንብና ልማድ ሥራውን አላገደውም፡፡ በዘመድና በወዳጅና በጠላት መካከል ልዩነት አላደረገም፡፡ እርሱን ያሳሰበውና ልቡን የነካው የሕይወት ውኃ የተጠማ ነፍስ ነበር፡፡ ማንንም የሰው ዘር አልናቀም፡፡ የእያንዳንዱ ነፍስ የመዳንን ፀጋ ሊያድል ፈለገ፡፡ ማንንም ቢያገኝ ለጊዜውና ለቦታው ገጣሚ የሆነ ትምህርት ይሰጥ ነበር: ሰዎች ጓደኞቻቸውን ሲንቁና ሲሰድቡ ሲያይ መለኮታዊ ዕርዳታ አንዳስፈለጋቸው ይገነዝብ ነበር:: ሕይወታቸው በብልግና የተበከሉትን ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ሊሆኑ መቻላቸውን እንዲያምኑ ተስፋ ሊያሳድርባቸው ይጥር በሰይጣን ወጥመድ ተይዘው መውጣት ያቃታቸውን ሰዎች ብዙ ጊዜ ያገኛቸው ለእንዲህ ያለው የወደቀ፤ ተስፋ የቆረጠ፣ ለታመመ፣በፈተና ለታጠረ ነፍስ የተገቢውን የርህራሄ ቃል ይናገረው ነበር፡፡ GWAmh 28.3

ሰከይጣን ጋር የጨበጣ ጦርነት የሚዋጉትንም አግኝቶአቸዋል፡፡ እነዚህን አርበኞች ድል እንደሚነሱ አረጋገጠላቸው፡፡ ምክኒያቱም የእግዚአብሔር መላዕክት ድል ሊያጐናጽፍአቸው በጐናቸው ተሰልፈው ነበር፡፡ GWAmh 28.4

ማንኛውም ሰው ወዳጁ መሆኑን ለማሳየት ከቀራሙች ጋር በአንድ ሞሰብ በላ:: ለተጠማው ልባቸው ቃሉ በረከትንና መርካትን አስገኙ:: ለእነዚህ ችላ ለተባሉና ለተናቁ የሕዝብ ክፍል የአዲስ ሕይወት ተስፋ ጐህ ቀደደላቸው የፈሪሣዊያንን ብክነት ለማረም የሱስ አይሁድ ሆኖ ከሣምራዊያን ጋር በአንድ ተቀላቀለ፡፡ በቤታቸው ውስጥ በአንድ አደረ፡፡ በአንድ ገበታ ከእነርሱ ጋር: በመንገዳቸውና በአደባባያቸው አስተማረ፡፡ በትህትና በአክብሮት ተመለከታቸው፡፡ ልክ ከእርሱ ጋር ሲገናኙ አይሁዶች የነፈገአቸውን የመዳን ተስፋ ሰጣቸው፡፡ GWAmh 28.5