የክርስቲያን አገልግሎት

82/246

መለኮታዊው መለኪያ

ያለማቋረጥ በሥራ ላይ የሚገኝ የጸባይ መለኪያ መሣሪያ አለ፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት ግብረገባዊውን ማንነት እየለኩና የሚያስፈልጎትን ነገር እያጣሩ ባህሪዎንም ሆነ አመለካከትዎን ወደ እግዚአብሔር ይመራሉ፡፡ --Review and Herald, April 2, 1889. ChSAmh 118.1

መሥራት ከምንችለው አንዲት ነቁጥ ያነሰ በመሥራታችን ላፊነቱን በግል እንወስዳለን፡፡ ጌታ አገልግሎት ለመስጠት ያገኘነውን እያንዳንዱን አጋጣሚ በትክክል ይለካል፡፡ ጥቅም ላይ ያልዋሉት ብቃትና ችሎታዎች በአገልግሎት የበለጸጉትን ያህል ተጠያቂነትን ያስከትላሉ፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንን መክሊቶች በትክክል የመጠቀም ኃላፊነት አለብን፡፡ የተሰጠንን ኃይል እግዚአብሔርን ለማክበር ባለመጠቀማችን ማድረግ ይኖርብን የነበረውን ያህል በፊቱ እንዳኛለን፡፡ ነፍሳችንን ባናጣም ነገር ግን እነዚያ ጥቅም ላይ ያላዋልናቸው መክሊቶች ያስከተሉትን ዘላለማዊ ውጤቶች እንገነዘባለን፡፡ ልናገኘው ሲገባ--ያላገኘነው ዕውቀትና ችሎታ ዘላለማዊ ዕጦት ያስከትላል፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 363. ChSAmh 118.2