የክርስቲያን አገልግሎት
ውሳኔ ሊሰጥ የግድ ነው
ጥቂት ለውጦች እንዲመጡ እየተጠባበቁ የነበሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦችን ተመልክቼ ነበር፡፡ በእነርሱ የሚጀምር አሰገዳጅ ኃይል ቢኖርም በመሳሳተቸው የተነሳ ተስፋ መቁረጥ ይደርስባቸዋል፡፡ አሁን በፈጣን እንቅስቃሴ ሥራውን ራሳቸው በመጀመር ስለ _ ሥራው እውነተኛውን ዕውቀት እንዲያገኙ በጽኑ ወደ እግዚአብሔር ማልቀሳቸው የግድ ይሆናል፡፡ ከፊት ለፊታችን እያለፉ ያሉት ትዕይንቶች እኛን ለማነሳሳትና የሚያደምጡ ሁሉ እውነትን በልባቸው እንዲያኖሩ ለማሳሰብ በቂ ኃይል ያላቸው ናቸው፡፡ የምድር መከር ለመድረስ ተቃርቦአል፡፡Testimonies, vol. 1, p. 261. ChSAmh 114.1
በሦስቱ መላእክት መልእክት እወጃ ባገኙት እውነት እንዴት ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ መቀደስ እንዳለባቸው ለሚያውቁ--በዩኒቨርስ ያለ ማንኛውም ነገር ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡ እያንዳንዱ የምናየውና የምንሰማው ነገር ተግባራችንን እንድናከናውን ይማጸነናል፡፡ እያንዳንዱ የሰይጣን ወኪሎች እንቅስቃሴ ክርስቲያኑ በተሰጠው ምድብ እንዲቆም ጥሪ የሚያደርግ ነው፡፡--Testimonies, vol. 9, pp. 25, 26. ChSAmh 114.2
የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በቅርቡ እውን እንደሚሆን የሚያበስረው መልእክት ለሁሉም የምድር ሕዝቦች መሰጠት ይኖርበታል፡፡ የእኛ ድርሻ ያለ እንቅስቃሴ መቀመጥ፣ ማንባትና እጆቻችንን ማፍተልተል ሳይሆን ከእንቅልፋችን ነቅተን ለጊዜውም ሆነ ለዘላለም ገጣሚ የሆነውን ሥራ መሥራት ነው፡፡--Southern Watchman, May 29, 1902. ChSAmh 114.3
“ችሎታችሁ የሚፈቅደውን ሁሉ ለመሥራት አሁኑኑ ወደ አገልግሎት ግቡ፤ መልአኩ ያለ ሥራ ለረጅም ጊዜ ሲቆይ ክንፎቹ እንዲንዘፈዘፉ እግዚአብሔርም ከመባረክ እንዲገታ ይሆናል”- Testimonies, vol. 5, p. 308. ChSAmh 114.4
ማንም ሰው እጆቹን አጣምሮ ያለ ሥራ የመቀመጥ ነጻነት እንዳለው አድርጎ አያስብ፡፡ ያለ አንዳች እንቅስቃሴ በስንፍና የተቀመጠው ይድናል ብሎ ማሰብ የማይመስል አባባል ነው፡፡ ክርስቶስ በምድራዊ አገልግሎቱ ያከናወናቸውን ተግባራት አሰብ ያድርጉ፡፡ ጥረቶቹ ሁሉ እንዴት ጽኑና የማይታክቱ ነበሩ! እንዲሠራው የተሰጠውን ሥራ ማንኛውም ነገር እንዲገታው አይፈቅድም _ ነበር፡፡ ዱካውን እየተከተልን ይሆን? Colporteur Evangelist, p. 38. ChSAmh 115.1
ነፍሳትን በማዳኑ ሥራ መለኮትና ሰብዓዊ ወኪሎች ጥምረት ፈጥረው ነበር፡፡ እግዚአብሔር የድርሻውን በመሥራቱ አሁን የክርስቲያኑ እንቅስቃሴ ይፈለጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ጥሪውን ያቀርባል፡፡ የእውነትን ብርሃን ተሸክመው ለሁሉም አገራት የማሠራጨቱን ድርሻ እንዲወጡ ሕዝቦቹን ተስፋ ያደርጋል፡፡ ከጌታ የሱስ ክርስቶስ ጋር አብሮ ለመሥራት ሽርክና የሚገባ ማነው?—Review and Herald, March 1, 1887. ChSAmh 115.2
ቤተ ክርስቲያን ሕያው እንድትሆን ከተፈለገ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ይኖርባታል፡፡ ተጻራሪ ይላት የሆኑትን ኃጢአትንና ስህተትን በሚቃወመው መሰረቷ ወይም በቀርፋፋው አካሄዷደስተኛ ልትሆን አይገባም፡፡ ይልቁንም የክርስቶስን ቀንበር መሸከም፣ ከመሪዋ ጋር መራመድና በጉዞዋ አዳዲስ ምልምሎችን ማፍራት ይጠበቅባታል፡፡ Review and Herald, Aug. 4, 1891. ChSAmh 115.3
ለውጊያው ለማነሳሳትና ለመገፋፋት ያለን ጊዜ አጭር ነው፡፡ ከዚያም ክርስቶስ ይመጣና የአመጹ ትዕይንት ድምዳሜ ያገኛል፡፡ የመጨረሻዎቹ ጥረቶቻችን ከክርስቶስ ጋር ለመሥራትና የእርሱን መንግሥት የማፋጠን ሥራ ለመሥራት ይውላሉ፡፡ በውጊያው የፊት ረድፍ ተሰልፈው የነበሩ አንዳንዶች ሰብሮ ለመግባት ጥረት ያደርግ የነበረውን የክፉ ኃይል በቀናኢነት እየተቋቋሙ፣ በግዳጅ ላይ እንዳሉ ቢወድቁም፤ ሌሎች የወደቁትን ጀግኖች በሐዘን ስሜት ከመመልከት ውጪ ሥራውን ለማቆም ጊዜ የላቸውም፡፡ አርማውን በሞት ከተለዩ እጆች ወስደው እውነትን ለሚደግፈውና ለክርስቶስ ክብር ለሚሰጠው _ አፍላ የታደሰ ኃይል መተላለፉ የግድ ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ--የጨለማ ኃይላትንና ኃጢአትን መቋቋም የግድ ይሆናል፡፡ ወቅታዊውን እውነት አምነው የተቀበሉ ንቁና ቆራጥ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ ጊዜው ይጠይቃቸዋል፡፡Review and Herald, Oct. 25, 1881. ChSAmh 115.4
በማንኛውም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ራሳቸውን ለእርሱ ቀድሰው በመስጠት የሚገኙበትን ሁናቴ ያገናዘበ ሥራውን የሚደግፍ ምርጥ አገልግሎት እንዲያበረከቱ ጌታ ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡-- Testimonies, vol. 9, p. 132. ChSAmh 116.1
ያለ ሥራ መቀመጥና ኃይማኖት እጅና ጓንት ሆነው መሄድ የማይችሉ እንደመሆናቸው፤ ለክርስትና ሕይወታችንና ተሞhሮአችን ብርቱ እጦት ዋንኛ መንስኤ ያለ እንቅስቃሴ መቀመጣችን ነው፡፡ አካላችን ተገቢውን እንቅስቃሴ ካላደረገ ጡንቻዎቻችን ደካማና የሰለሉ የመሆናቸው እውነታ ለመንፈሳዊው ተፈጥሮም በተመሳሳይ ይሠራል፡፡ አንድ ሰው ጠንካራ መሆን ከፈለገ በውስጡ ያለውን ኃይል ማንቀሳቀሱ የግድ ነው፡፡--Review and Herald, March, 13, 1888. ChSAmh 116.2
ያለ ሥራ የሚቀመጥ ሰው ህይወት አሰቃቂ እንደመሆኑ ትጉ ሠራተኞች መሆን ይጠበቅብናል፡፡ ክርስቶስ ፍጸሜ እንዲያገኝ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ለሰጠበት ታላቅ አገልግሎት፤ ያለ ሥራ ለመቀመጣችን ምን ዓይነት ምክንያት ማቅረብ እንችል ይሆን? መንፈሳዊው ሕይወታችን እንቅስቃሴ ቢስ በሆነ ቁጥር መኖሩን ያቆማል፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎች እንዲጠፉ የሚመኘው የሰይጣን የተቀነባበረ ዘዴ ነው፡፡ መላው ሰማይ ሕዝቡን ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት በማዘጋጀት ሥራ ተጠምዶአል፡፡ “እኛ ሁላችን ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች ነን፡፡” የሁሉም ነገር ፍጻሜ ተቃርቦአል፡፡ አገልግሎት የመስጠት ዕድሉ ያለን አሁን ነው፡፡--Review and Herald, Jan. 24, 1893. ChSAmh 116.3
ርኅራኄ የተላበሰ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ወንጌላውያን ይፈለጋሉ፡፡ አልፎ አልፎ የሚደረጉ ጥረቶች ሊያመጡ የሚችሉት ውጤት አነስተኛ በመሆኑ ትኩረትን ልንስብና ጥልቅ በሆነ ጽናት ልንሠራ ይገባል፡፡, -Testimonies, vol. 9, p. 45. ChSAmh 117.1
ጊዜ ወስደው ቢያጤኑ እግዚአብሔር በሰጣቸው መክሊቶች አንዳችም እንዳላበረከቱ መመልከት የሚችሉ፤ ኃጢአተኛ ቸልተኝነት ያሳዩ በመካከላችን አሉ፡፡- Testimonies, vol. 6, p. 425. ChSAmh 117.2
በዓለም ላይ ያለን አቋም ምን ይመስላል? ጊዜውን እየተጠባበቅን ብንገኝም፤ ሆኖም ይህ ጊዜ ለረቂቅና በተግባር ላልተፈተነ አምልኮ መዋል የለበትም፡፡ መጠባበቅ፣ መከታተልና በንቃት መሥራት ጥምረት ሊያገኙ ይገባል፡፡ ሕይወታችን ግላዊ ቅድስናችንንና እግዚአብሔር የሚጠይቀንን አገልግሎት ቸል ብሎ በዓለማዊ ነገሮች የተጣደፈና የሚነዳ መሆን የለበትም፡፡ በሥራችን ሰነፍ መሆን እንደሌለብን ሁሉ ጌታንም በጋለ መንፈስ ማገልገል ይኖርብናል፡፡ የነፍሳችን መብራት ጥሩ ሆኖ የሚያበራና መቅረዛችን በጸጋው ዘይት የተሞላ ይሁን፡፡ መንፈሳዊ ዝቅጠት ገጥሞን የጌታ ቀን እንደ ሌባ እንዳይመጣብን ቅድመ ጥንቃቄ ልናደርግ የግድ ነው፡፡ -- Testimonies, vol. 5, p. 276. ChSAmh 117.3
አንዳችም መንፈሳዊ ሥራ ፈትነት ሊኖር በማይገባው ዘመን ውስጥ እየኖርን እንገኛለን፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ በሰማያዊው የሕይወት የኃይል ሞገድ ላይ ሊለኮስ ይገባል፡፡Testimonies, vol. 8, p. 169. ChSAmh 117.4
ምድራዊው ሕይወትዎ መሥራት በሚችሏቸው በጎ ነገሮች የታጨቀ ይሁን፡፡Testimonies, vol. 5, p. 488. ChSAmh 117.5
የሱስ በስሙ የሚያምኑ ሁሉ ጽኑ ሠራተኞች እንዲሆኑ ይሻል፡፡ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል በየሱስ ክርስቶስ ዐለት ላይ መገንባቱ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ በተቻለ መጠን የእያንዳንዱ መንፈሳዊ ሕይወት የተገነባበትን መሰረት የሚነቀንቅና የሚፈትን ማዕበል ይነሳል፡፡ የአሸዋውን መሰረት አስወግደን ዐለቱን እንፈልግ፡፡ መሰረቱን ከመጣላችን በፊት በጥልቀት መቆፈራችንን እርግጠኞች እንሁን፡፡ ዘላለማዊውን ግንብ እንገንባ! በእንባና ከልብ በመነጨ ጸሎት እንገንባ፡፡ ከዚህ በኋላ የእያንዳንዳችሁ ሐይወት ባማሩ ሥራዎች ያጌጡ ይሁኑ፡፡ በእነዚህ የመጨረሻ ዘመናት እንደ ካሌብ ያሉ አያሌዎች በእጅጉ ይፈለጋሉ፡፡-Testimonies, vol. 5, pp. 129, 130. ChSAmh 117.6