የክርስቲያን አገልግሎት
መመሪያን ከሁናቴዎች ጋር ስምሙ አድርጎ መውሰድ
በእግዚአብሔር ሥራ ጠቃሚ ከሆኑና መልካም ሥብዕና ከተላበሱ ሠራተኞች መካከል እጅግ ትህትናና ዝቅ ማለትን ለሚጠይቀው አገልግሎት ሥልጠና የወሰዱ ምን ይህሉ ይሆኑ! ሙሴ ግብጽን ለማስተዳደር ተስፋ የተጣለበት መሪ ቢሆንም ነገር ግን እግዚአብሔር ለሾመው ሥራ ከነበረበት ቤተ መንግሥት ቅጥር አልወሰደውም፡፡ ይልቁንም አርባ ዓመታት በታማኝነት በእረኝነት ካገለገለ በኋላ ሕዝቡን ነፃ እንዲያወጣ ተላከ፡፡ ጌዴዎን የእግዚአብሔር መሣሪያ ሆኖ ሕዝቡን ነፃ እንዲያወጣ የተወሰደው ስንዴ ይወቃበት ከነበረው አውድማ ነበር፡፡ ኤልያስ የእርሻ ሥራውን ትቶ የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲታዘዝ ጥሪ ቀረበለት፡፡ አሞጽ የሚያውጀው መልእክት በእግዚአብሔር እስኪሰጠው ድረስ አራሽ ገበሬ _ ነበር፡፡ ከክርስቶስ ጋር የሚሠሩ ሁሉ ውጣ ውረድ የበዛውንና አልጋ ባልጋ ያልሆነውን አገልግሎት እንደሚያበረክቱ ሁሉ የሚሰጧቸው ትምህርቶችና መመሪያዎች በማስተዋል ሊመረጡ፣ ከአገልጋዩ ጸባይና ያለማቋረጥ ከሚሠራቸው ሥራዎች ጋር እንዲስማሙ ሆነው ሊወሰዱ ይገባል፡፡Gospel Workers, pp. 332, 333. ChSAmh 83.3