የክርስቲያን አገልግሎት

56/246

ልዩ ሥልጠና

የጤና ተሐድሶ መርኅዎችን ለሰዎች ለማስተማር ከፍተኛ ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡ ለምግብ ዝግጅት አገልግሎት የሚውል የማብሰያ ክፍል ሊዘጋጅና ጤናማ ምግቦች እንዴት እንደሚሠሩ የቤት ለቤት የማስተማር ሥራ መከናወን ይኖርበታል፡፡ ወጣቱም ሆነ አዛውንቱ ስለ ምግብ ዝግጅት ተገቢ ትምህርት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የእውነት መልእክት በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ምዕመኑ ቀለል ያለና የምግብ ፍላጎት የሚከፍት ማዕድ ማዘጋጀት በሚችልበት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሊሠራ ይገባል፡፡ ከሥጋ ውጪ ያሉ ምግቦች--እንደ እህል፣ ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ለጤና ያላቸው ፋይዳ አጽንኦት ተሰጥቶ ለታዳሚው ሊገለጥ ይገባል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 161. ChSAmh 83.1

የጤናን መርኅዎች ተከትለው ለመኖር የሚመኙ ጥቅም ላይ ሊያውሏቸው የሚችሏቸው ቀለል ያሉ ጤናማ ምግቦች አዘገጃጀት ዙሪያ ቤተ hርስቲያን ባለበችበት ስፍራ ሁሉ መመሪያ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የተቀበሏቸውን ብርሃኖች ለጎረቤቶቻቸው ሊያካፍሉ ይገባል፡፡-Gospel Workers, p. 362. ChSAmh 83.2