የክርስቲያን አገልግሎት
ምዕራፍ 5—ቤተ ክርስቲያን ማሰልጠኛ ማዕከል
ወቅቱ የሚሻው አንገብጋቢ ጉዳይ
ለጌታ ሥራ ጥቅም ላይ እንዲውል ተገቢው ትምህርትና ሥልጠና ሊሰጠው የሚገባውን፣ ቤተ ክርስቲያኖቻችንን ለማጎልበት በእጅጉ የሚያስፈልገውን የምዕመናንን መክሊት ለይተው በመረዳት ኮትኩተው ማሳደግ የሚችሉ አስተዋይና ትጉ ሠራተኞች በዚህ ወቅት ያስፈልጋሉ፡፡ አባላት የቤተ ክርስቲያንን ተልdኮ ለማራመድም ሆነ አማኝ ላልሆኑ ሕዝቦች ሊሰጡ ስለሚገባው አገልግሎት ትምህርት የሚሰጡት ሠራተኞቻችን ወደ ትላልቆቹም ሆነ አነስተኞቹ በመላው _ አብያተ ክርስቲያኖቻችን ለመመደብ የሚያስችል በጥሩ ሁናቴ የተነደፈ እቅድ ሊኖር ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖችን በመጎብኘት የሚሠሩ ሁሉ ወንድም እህቶች የወንጌልን ሥራ እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ሊረዷቸው የሚችሉ ተጨባጭ ዘዴዎችንና መመሪያዎችን ማካፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ -- Testimonies, vol. 9, p. 117. ChSAmh 80.1
ቤተ ክርስቲያን አባላቶቿን በዲሲፕሊን አንጻና ለዓለም ለምትገልጸው መልእክት ብቁ ሆና ትገኝ ዘንድ እግዚአብሔር እየጠበቃት ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር ሐዝቦች የከበረ ዋጋ ያላቸውን መክሊቶቻቸውን ገልጠው ሥራ ላይ ማዋል የሚያስችላቸው ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ሰዎች እነዚህን መክሊቶቻቸውን ሲጠቀሙ የመታመንና ተጽእኖ የማሳደር፣ ንጽህናን ጠብቆ የማቆየትና መርኅዎችን ከእርክስና የመጠበቅ እመርታ ያሳያሉ፡፡ ይህ ሲሆን ታላቅና መልካም ክንውን ለጌታ እናስገኛለን፡፡-Testimonies, vol. 6, pp. 431, 432 ChSAmh 80.2
እያንዳንዱ ሠራተኛ ሥራውን በሚገባ ያስተዋለ ቅልጥፍናና ብቃት ሲላበስ እውነትን በየሱስ እንደተስተዋለው ከፍታና ስፋት ማቅረብ ይችላል፡፡--Testimonies, vol. 7 p. 70. ChSAmh 81.1
የቤተ ክርስቲያን አባላትን ለማስተማር የሚረዳውን ይህን በጥሩ ሁኔታ የተዋቀረ እቅድ ለመተግባር አንዳችም መዘግየት ሊኖር አይገባም፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 119. ChSAmh 81.2
ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር እንዲሠራ፣ በአገልጋዮች ሳይሆን በእርሱ ላይ ብቻ እንዲተማን ማስተማር ለሕዝባችን ልንለግሰው የሚገባ ታላቁ እርዳታ ነው: -Testimonies, vol. 7, p. 19. ChSAmh 81.3
እስከ ዛሬ የተሰበኩት ስብከቶች ሰፊና ራሱን የካደ የሠራተኛ መደብ አለመፍጠራቸው እሙን ነው፡፡ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ብርቱ ውጤቶችን ከማስመዝገብ አኳያ ሊታይ ይገባል፡፡ ዘላለማዊ ተስፋችን አደጋ ላይ ወድቆአል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖች ብርሃን ለማስራጨት የሚያስችላቸውን መክሊቶች ከመጠቀም በመሰናከላቸው እየተመናመኑ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ብርሃኑን አብርቶ በተጨባጭ እንዲጠቀምበት የሚያስችል ከመምህሩ የተለገሱ ዓይነት ትምህርቶችጥንቃቄ በተሞላው መመሪያ ሊሰጡ ይገባል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 431. ChSAmh 81.4
የእግዚአብሔር ሕዝብ አያሌ ስብከቶች ተሰብከውለታል፡፡ መልእክቶቹ ክርስቶስ ለሞተለት ሰብዓዊ ዘር መመስከር እንደሚኖርብን የሚያስተምሩን ናቸውን? _ አማኞች አገልግሎት የሚጡበት መንገድ ተቀይሶላቸው እያንዳንዳቸው የሥራው ተካፋይ የመሆናቸውን አስፈላጊነት መመልከት ችለው ይሆን?— Testimonies, vol. 6, p. 431. ChSAmh 81.5
ሰዎች ሳይታሰብ ሊከሰት ለሚችል አስቸኳይ ሁኔታ ብቁ ሆነው መገኘት የሚችሉት ትምህርትና ተግባራዊ ልምምድ ሲኖራቸው እንደመሆኑ፤ እያንዳንዱ ሰው የሚሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ተሸክሞ ተገቢውን ልምድ እንዲያካብት--ከተሰጠው መክሊት ጋር ገጣሚነት ያለው አገልግሎት ላይ ለመመደብ የሚያስችል በሳል ዕቅድ የማውጣት ሥራ መሠራት ይኖርበታል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 221. ChSAmh 82.1