የክርስቲያን አገልግሎት

53/246

ከኤልያስ ተሞhሮ የሚቀሰሙ ትምህርቶች

ተስፋ መቁረጥና ግልጽ ሽንፈት ከተስተዋለባቸው ከእነዚያ ኤልያስ ካለፈባቸው ጊዜያቶች የምንማራቸው አያሌ ትምህርቶች አሉ፡፡ ሰዎች ትክክለኛውን መንገድ ርግፍ አድርገው ትተው ሲሄዱ ከተስተዋለበት ከእንዲህ ያለው ተሞክሮ በዘመናችን የሚገኙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በዋጋ ሊተመን የማይችል ተምህርት ማግኘት ይችላሉ፡፡ ዛሬ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ የሚገኘው ክህደት በነቢዩ ዘመን በመላው እስራኤል ተሰራጭቶ ከተስተዋለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ዛሬ ሰዎች ሰብዓዊውን ፍጡር ከእግዚአብሔር በላይ እያሞጋገሱ፣ ለታዋቂ መሪዎች (ለሰው ሊሰጥ ከሚገባው በላይ) ክብርና ውዳሴ እየሰጡ፣ ለዚህ ዓለም ሐብት እየሰገዱና በእግዚአብሔር ቃል ላይ ከተገለጸው እውነት የበለጠ ዋጋ ለሳይሳዊው አስተምህሮ እየሰጡ በዓልን እያመለኩ ይገኛሉ፡፡ በክፋት የተሞላው ጥርጣሬና አለማመናቸው በሰዎች ልብና አእምሮ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ በመሆኑ ብዙዎች ሰብዓዊውን ንድፈ ሐሳብ በእግዚአብሔር እየተኩ ይገኛሉ፡፡ ከአምላካዊው ቃል በላይ ለሰብዓዊው አስተምህሮ አጽንኦት የሚሰጥበት ወቅት ላይ መድረሳችን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕግና አምላካዊው የጽድቅ መለኪያ ፋይዳ ቢስ መሆኑ በይፋ እየተነገረ ነው፡፡ ወንዶችና ሴቶች ሰብዓዊ ተቋማትን በእግዚአብሔር ቦታ እንዲተኩና ስለ ሰብዓዊው ፍጡር ደስታና ደኅንነት ሲባል የታቀደውን እንዲረሱ ለማድረግ የእውነት ጠላት የሆነው አሳች ኃይሉን ተጠቅሞ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ወደ ፊት በብዙ ቦታ እንደሚሰራጭ የሚጠበቀው ይህ የክህደት ተግባር ዓለማቀፍ ገጽታ አይኖረውም፡፡ ሁሉም የምድር ነዋሪዎች ሕገ ዐልባና ኃጢአተኛ አይሆኑም፡፡ እግዚአብሔር--ስለ ክርስቶስና ሕጉ በሙላት ለማወቅ አጥብቀው የሚናፍቁና የሚሹ፣ ክርስቶስ በቅርቡ ተገልጦ የኃጢአትንና ሞትን ሥልጣን ድል እንደሚመታ በተስፋ ላይ ተስፋ የሰነቁ—ለበዓል ያልሰገዱ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሕዝቦች አሉት፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ባለማወቅ በዓልን እያመለኩ የሚገኙትን አያሌ ሕዝቦች ለመመለስ አሁንም እየጣረና እየታገለ ይገኛል፡፡Prophets and Kings, pp. 170, 171. ChSAmh 78.4