የክርስቲያን አገልግሎት
ምድርን ደግፎ የያዘው የአምላካዊ መንፈስ መነሳት
ይህችን ምድር ደግፎ የያዘው የእግዚአብሔር መንፈስ ቀስ በቀስ እየተዋትና እየለቀቃት ይገኛል፡፡ ማዕበል፣ ወጀብ፣ ሰደድ እሳት፣ ጎርፍ-በምድርም ሆነ በባሕር ላይ የሚደርሱ ውድመቶች አንዱ ሌላውን በፍጥነት እየተከተለ ይገኛል፡፡ ሳይንስ ለእነዚv ቀውሶች ትንተና ለመስጠት አጥብቆ ይሻል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ መምጫ መቃረብን የሚነግሩን እነዚህ ዙሪያችንን የከበቡን ብርቱ ምልክቶች ሌላ ሳይሆኑ የእውነተኛው መንስኤ መለያ ባvሪዎች ናቸው፡፡ አራቱን ነፋሳት የያዙት መላእክት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ታትመው እስኪያበቁ እንደማይለቋቸው ሰዎች በቅጡ ለይተው መገንዘብ አይችሉም፡፡ ነገር ግን መላእክቱ ነፋሳቱን እንዲለቅቁ እግዚአብሔር ሲያዛቸው የትኛውም ብዕር ሊገልጸው የማይችል አሰቃቂ ሁከት ይሆናል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 408. ChSAmh 71.1
ዛሬ እየተመላለስንባቸው ያሉ ቀናት የተከበሩና አስፈላጊ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ቀስ በቀስ ምድርን ለቅቆ መሄዱ እሙን ነው፡፡ አምላካዊውን ጸጋ በሚንቁ ላይ መቅሰፍቶች እየወረዱ ፍርድም እየተሰጠ ነው፡፡ በየብስም ሆነ በባሕር ላይ የሚወርዱ መቅሰፍቶች፣ የማኅበረሰቦች ውጥረት ውስጥ መግባትና ውጊያ ሊቀሰሱ የሚችሉ ማስጠንቀቂያዎች እንደሚከሰቱ አስቀድሞ ተመልክቶአል፡፡ ከባድና አስቸጋሪ ሁናቴ ከፊት ለፊታችን እንደተደቀነ ተተንብዩልናል፡፡ የክፉው ኃይላት ለመጨረሻው ውድመትና ጥፋት ከወዲሁ ኃይላቸውን በአንድ እያጣመሩና እየተጠናከሩ ይገኛሉ፡፡ በዓለማችን በቅርቡ ግዙፍ ለውጦች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ በስተመጨረሻ እውን የሚሆኑ እንቅስቃሴዎች ፈጣንና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈጸሙ ናቸው::--Testimonies, vol. 9, p. 11. ChSAmh 71.2
ሰብዓዊ ማስታገሻ ወይም ፈውስ የማይገኝለት ሐዘን በምድር ላይ የሚንሰራፋበት ጊዜ እጅግ ተቃርቦአል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ምድርን እየተዋት ነው፡፡ በባሕርና በምድር ላይ የሚደርሱ ውድመቶች አንዱ ሌላውን እየተከተለ በፍትነት ገቢራዊ ይሆናሉ፡፡ የሰውን ሕይወት በከፍተኛ መጠን የሚቀጥፈውንና መጠነ ሰፊ ንብረት የሚያወድመውን የመሬት መንቀጥቀጥ፣ አውሎ ነፋስ፣ ማዕበል፣ ሰደድ እሳትና ጎርፍ በምን ያህል ፍጥነት እንሰማ ይሆን! እነዚህ የተፈጥሮ ኃይላትን መቃወስ ይፋ እያደረጉ በፍጥነት የሚቀያየሩ መቅሰፍቶችሙሉ ለሙሉ ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጪ ሲሆኑ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ዓላማ በውስጣቸው ይነበባል፡፡ የተፈጥሮ ኃይላት መቃወስወንዶችና ሴቶች የሚገኙበትን አደጋ አስተውለው ወደ ህሊናቸው እንዲመጡ እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው የመቀስቀሻ መሣሪያዎቹ አካል ናቸው፡፡--Prophets and Kings, p. 277. ChSAmh 72.1