የክርስቲያን አገልግሎት

45/246

ዘመናት ያስቆጠረው ምስቅልቅል

አያሌ ዘመናት የፈጀውን ውጥንቅጥ ተከትሎ የምድር ታሪክ መደሚያ በራፍ ላይ ቆመናል፡፡ የእሳት ቃጠሎ፣ጎርፍ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጦርነትና ደም መፋሰስ እየተከታተሉ በፍጥነት በመከሰት የአምላካዊውን ፍርድ እውን መሆን ያመላክታሉ፡፡ ከዚህ በኋላ የምህረት መልአክ ንስሐ ላልገቡት ጥአን መከታ ሆኖ መቆየት ስለማይችል ተግባራዊ ሊሆኑ በሚችሉ ታላላቅና ወሳኝ ክስተቶች መደነቅ አኖርብንም፡፡— Prophets and Kings, p. 278. ChSAmh 69.2

አስጊው ሁናቴ ውሎ አድሮ በእያንዳንዳችን ላይ እንደ ሌባ እያደባ ነው፡፡ ጸሐይ ብርሃንዋን መፈንጠቋንሰማያትም የእግዚአብሔርን ክብር ማወጃቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡ ሰዎች ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይተክላሉ፣ ቤት ይሠራሉ፣ ይጋባሉ፡፡ ነጋዴው ይገዛል፣ ይሸጣል፡፡ አንዱ ሌላውን ገፍቶ እየጣለ- ከፍ ላለው ቦታ የሚደረገው ትንቅንቅና ሽኩቻ እንደ ደራ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ደስታ ወዳዶች የቴአትር ቤት ደጃፎችንና የቁማር መጫወቻ ስፍራዎችን እንዳጣበቡ ነው፡፡ ደስታው ወደ ጡዘት እያመራ--የምኅረት ሰዓት በፍጥነት እየደረሰ ነው፡፡ እያንዳንዱ ጉዳይ ባለበት ሁናቴ ለዘላለም ተወስኖ ሊቀር ነው፡፡ ሰይጣን የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ይመለከታል፡፡ ወኪሎቹን ተጠቅሞ ሰዎች እንዲስቱ፣ እንዲሞኙ፣ ጊዜ እንዳይኖራቸውና በምድራዊው ነገር ብቻ እንዲመሰጡ በማድረግ የምኅረት ጊዜ አብቅቶ ለዘላለም የይቅርታ ደጃፍ እንዲዘጋባቸው እየሠራ ይገኛል፡፡Southern Watchman, Oct. 3, 1905. ChSAmh 69.3

አምላካዊውን ሕግ መተላለፍ ገደቡ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ዓለም ተደናግራለች፡፡ በቅርቡ ብርቱ ሽብር የሚለቅ ክስተት በሰብዓዊው ፍጡር ላይ ይደርሳል፡፡ መጨረሻው እጅግ ተቃርቦአል፡፡ እኛ እውነትን የምናውቅ መላውን ምድር ከዳር እስከ ዳር ለሚያናውጠው ክስተት ከወዲሁ ልንዘጋጅ ይገባል፡:Testimonies, vol. 8, p. 28. ChSAmh 70.1

የምድር በኃጢአትና እርክስና መውደቅ ታላቁና የመጨረሻው አስከፊ ነውጥ በደጃፍ መሆኑን ያሳየናል፡፡ በእግዚአብሔር ሕግ ላይ የሚደርሰው ጥሰት ዓለማቀፋዊ ገጽታ ሲላበስና ሐዝቦቹ ላይ የገዛ ወገኖቻቸው በደልና መከራ ሲያደርሱበዚያን ጊዜ ጌታ ጣልቃ ይገባል፡፡-- Christ’s Object Lessons, p. 178. ChSAmh 70.2

ታላላቅና የተከበሩ ክስተቶች የሚጀምሩበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ትንቢቶች ፍጻሜ እያገኙ ነው፡፡ እንግዳና በድርጊት የተሞሉ ታሪኮች በሰማይ መዝገብ ላይ እየሰፈሩ ነው፡፡ በዓለማችን የሚገኝ እያንዳንዱ ነገር ታውኮአል፡፡ ጦርነቶች ይካሄዳሉየጦርነት ወሬዎችም ይሰማሉ፡፡ ሕዝቦች በቁጣ ተሞልተዋል፤ ሙታን የሚፈረዱበትም ጊዜ ደርሶአል፡፡ የእግዚአብሔር ቀን በቶሎ ይመጣ ዘንድ ምድራዊ hስተቶች ፈጥነው በመለዋወጥ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የሚቀረው እጅግ አነስተኛ ጊዜ ነው:፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣hርስቲያኑ አገልጋይ የሚጋፈጣቸው የዓለም ሁናቴዎች መንግሥት በመንግሥት ላይ ሲነሳ እንጂ እርስ በርስ ትስስር ሲፈጥሩ እየተመለከትን አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በግንባራቸው ላይ እስከሚታተሙ ድረስ አራቱ ነፋሳት አይለቀቁም፡፡ ከዚህ በኋላ የምድር ኃይላት ለታላቁ ውጊያ ጉልበታቸውን በአንድ ያስተባብራሉ፡፡-- Testimonies, vol. 6, p. 14. ChSAmh 70.3