የክርስቲያን አገልግሎት

31/246

የመነቃቃትና ተሐድሶ አስፈላጊነት

ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት በማጥናትና ራሳቸውን ከአምላካዊው ቃል አስተምህሮ ጋር ስምሙ በማድረግ መላውን ዓለም አስደምሞ በቅርቡ እውን ለሚሆነው ሰበር ክስተት ሊዘጋጁ ይገባል. . . እግዚአብሔር መነቃቃትና ተሐድሶ እንድናደርግ ጥሪ ያቀርብልናል፡፡-Prophets and Kings, p. 626. ChSAmh 55.1

ከማንኛውም ነገር በላይ ታላቁና በእጅጉ የሚያስፈልገን እውነተኛ እግዚአብሔርን የመምሰል መነቃቃት ነው፡፡-Review and Herald, March 22, 1887. ChSAmh 55.2

በጥንቃቄ የተሞላ ጥብቅ መነቃቃት የምናደርግበት ጊዜውመጥቶአል፡፡ ይህ ተሐድሶ በሚጀምርበት ወቅት የጸሎት መንፈስ እያንዳንዱን አማኝ ስለሚነቃቃ ግጭትና አለመስማማት ከቤተ hርስቲያን ይወገዳል፡፡--Testimonies, vol 8, p. 251. ChSAmh 55.3

ሁለት የተለያዩ ነገሮች የሆኑት መነቃቃትና ተሐድሶ በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍና ጥንቃቄ ሊተገበሩ ይገባል፡፡ መነቃቃት--በመንፈሳዊው ማንነት ላይ ህይወት መዝራት፣ የአእምሮንና የልብን ኃይል መቀስቀስ፣ በመንፈሳዊ ሞት ላይ ሥርየት ማግኘት ሲሆን ተሐድሶ ደግሞ--መልሶ ማደራጀት፣ የጽንሰ ሐሳቦች፣ የንድፈ ሐሳቦች፣ የልምድና የተሞክሮዎች ለውጥ ነው:: ተሐድሶ ከመንፈሳዊ መነቃቃት ጋር መገናኘት ካልቻለ በቀር መልካሙን የጽድቅ ፍሬ ማፍራት አይችልም፡፡ መነቃቃትና ተሐድሶ የተቀመጠላቸውን ተግባር በማከናወን የታለመውን ውጤት ማስገኘት ይችሉ ዘንድ ኅብር መፍጠራቸው የግድ ነው፡፡-- Review and Herald, Feb. 25, 1902. ChSAmh 56.1

መጽሐፍ ቅዱስ እስካሁን ከተመለከትነው የላቀ ንጹህና ቅዱስ ሥራ እንድንሠራ አይጠይቀን ይሆን?. . . ራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ለማስገዛት ፈቃደኛ የሆኑ ወገኖች ብልሐትና ጥንቃቄ የሚጠይቀውን የተሐድሶ ተግባር እንዲመሩ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡ ከፊታችን አስጊ ሁናቴና ችግር እንደተደቀነ እመለከታለሁ፡፡ ሁሉም በጽናት እንዲቆም ጌታ ለሠራተኞቹ ጥሪ ያቀርባል፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ ካለፉት ዓመታት ይልቅ ዛሬ ጥልቅ በሆነና በእውነተኛ ቅድስና ለእግዚአብሔር ሊቆም ይገባል. . . በቅርቡ በጨለማው ጊዜያት ከፊት ለፊቴ ባለፉት ትዕይንቶች በእጅጉ ተነክቼአለሁ፡፡ ወቅቱ በሁሉም አቅጣጫ ብርቱ መነቃቃትና ታላቅ እንቅስቃሴ የታየበት ይመስል ነበር፡፡ ሕዝባችን ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ በመስጠት በቀናው ጎዳና ሲተም ተስተውሎአል፡፡--General Conference Bulletin, May 29, 1913, p. 34. ChSAmh 56.2

በእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል ታላላቅ ተሐድሶዎችን ያደረጉ ራእዮችከፊት ለፊቴ ሲያልፉ ተመልክቼአለሁ፡፡ _ አብዛኞቹ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ውዳሴ ያቀርቡ ነበር፡፡ በሽተኞች ፈውስ ያገኙ ሲሆን ሌሎች ተአምራቶችም ተደርገዋል፡፡ ወገኖች በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን ሲጎበኙና የእግዚአብሔርን ቃል ሲገልጡላቸው ተመልክቼአለሁ፡፡ ልቦች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመነካታቸውና በደለኝነታቸውን መመልከት በመቻላቸው ጽኑና እውነተኛ መለወጥ ተስተውሎ ነበር፡፡ እውነትን ለማወጅ የሚያስችሉ ደጃፎች በየአቅጣጫው ወለል ብለው በመከፈታቸው ዓለም በሰማያዊው ተጽእኖ ወገግ ያለች ትመስል ነበር፡፡ እውነተኞቹና ትሑታን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ታላላቅ በረከቶችን ተቀብለው ነበር፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 126. ChSAmh 57.1

በእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል ተሐድሶ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የምትገኝበት ሁናቴ ሕይወቱን ለእኛ የሰጠውን እርሱን በትክከል የሚወhል ስለ መሆኑ ለመመርመር አይገፋፋን ይሆን?-- Testimonies, vol. 3, p. 474. ChSAmh 57.2

የስንፍናና የአኬተኝነት ተችቶች ከቤተ ክርስቲያን ተጠራርገው ሲወገዱ ግርማ የተላበሰው የጌታ መንፈስ ተጋግሎ ይታያል፡፡ መለኮታዊው ኃይል ይገለጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሰራዊት ጌታ በጎነት የሆነውን የሥራውን ክንውን ትመለከታለች፡፡ ብርቱ የእውነት ብርሃን ጨረሮች ግልጽና ደማቅ ሆነው ስለሚያንጸባርቁ በሐዋርያት ጊዜ እንደሆነው አያሌ ነፍሳት ከስህተት ወጥተው እውነትን ይቀላቀላሉ፡፡ ምድር ከጌታ ክብር የተነሳ ታበራለች፡፡-- Testimonies, vol. 9, p. 46. ChSAmh 57.3