የክርስቲያን አገልግሎት
ከሃያ ሰዎች መሃል አንዱ እንኳ አልተዘጋጀም
ለቤተ ክርስቲያን በሰጠሁት የተከበረ መልእከት—በአባልነት የባሕር መዝገብ ላይ ስማቸው ከሰፈረና ምድራዊ ታሪካቸው ሊደመደም ከተቃረበ ሃያ ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ ባለመዘጋጀቱ እንደ ማንኛውም በዓለም ያለ ተራ ኃጢአተኛ ያለ እግዚአብሔርና ያለ ተስፋ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ወገኖች እግዚአብሔርን እያገለገሉ ቢሆንም--ምድራዊው ሐብትና ንብረት ጣኦት ሆኖባቸዋል፡፡ ይህ በግማሽ ልብ መዋለል ወደ ክርስቶስ የሚያቀርብ ሳይሆን ያለማቋረጥ በእርሱ ላይ የሚደረግ የክህደት ተግባር ነው፡፡ ብዙዎች ያልተገራውንና በቁጥጥር ስር ያልዋለውን የገዛ መንፈሳቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘው መጥተዋል፡፡ መንፈሳዊ ምርጫቸው ግብረገብ በጎደለው ማንነታቸው የተጣመመና የረከሰ፣ ውስጣዊውም ሆነ ውጫዊው የክርስትና ሕይወታቸው በማጭበርበር የተሞላ፣ ራሳቸውን ለሴሰኝነት አሳልፈው የሰጡና በመንፈሳቸው፣ በዓላማቸውም ሆነ በልባቸው ይህን ዓለም የሚወክሉ ናቸው፡፡ በኃጢአት ውስጥ እየተመላለሱ ክርስቲያኖች ነን ይላሉ! ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ክርስቲያን ቆጥረው ለክርስቶስ ምስክር ሆነው የሚመላለሱ ወገኖች ከእነዚህ መሃል ወጥተው የረከሰውን ከመንካት እንዲቆጠቡ፣ እንዲለዩ ይጠየቃሉ... ጌታ ወደ ኋላ ያፈገፈጉ፣ የደረቁ አጥንቶችሕዝቦቹ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ የሕይወት እስትንፋሱን እንዲሰጣቸው ብዕሬን ዝቅ፣ ነፍሴን በጸሎት ከፍ አድርጌ እማጸነዋለሁ፡፡ ሌባ ጨለማን ተገን አድርጎ በቅጡ ሳይስተዋልና ኮሽታ ሳያሰማ ባልተዘጋጁትና ባንቀላፉት ላይ በድንገት እንደሚመጣ—ፍጻሜውም እንዲሁ ተቃርቦአል፡፡ ወገኖች እንደ ሌሎች ማንቀላፋታቸውን ትተው ተግተውና ራሳቸውን ተቆጣጥረው ጠባበቁ ዘንድ ጌታ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በምቾት የሚገኘውን ልባቸውን ይንካ፡፡General Conference Bulletin, 1893, pp. 132, 133. ChSAmh 54.3