የክርስቲያን አገልግሎት
የላፊነት ክፍተት የሚሞሉ ተተኪዎች
አያሌ መንፈሳዊ ኃላፊነቶችን ተሸክመው የኖሩ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በሞት እየተነጠቅን ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን እንደ ሕዝብ በእኛ የተጀመረው ተሐድሶ እንዲቀጥል ቀዳሚ ሚና የነበራቸውአሁን አፍላ የአገልግሎት ዘመናቸውን እያለፉ አካላዊም ሆነአእምሮአዊ ብቃታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየቀነሰ ይገኛል፡፡ ከጉዳዩ አሳሳቢነት አኳያ—የእነርሱን ቦታ ማን ይሞላዋል? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ የዛሬዎቹ ብቃት ያገኙ ብርሃን ተሸካሚዎች በሚያርፉ ጊዜ—ይህ በእጅጉ አስፈላጊና ወሳኝ ትኩረት የሚሻው የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ለእነማን ይሰጣል? እኛ አንችልም ነገር ግን የዛሬዎቹ ወጣቶች እነዚህን ሸክሞች እንዲወስዱ በጉጉት ልንመለከታቸውና ኃላፊነት ሊወድቅባቸው ይገባል፡፡ ሌሎች ትተዉላቸው ያለፉትን ሥራ እነዚህ ሊወስዱ የግድ ነው፡፡ በግብረገብ የታነጹ፣ ኃይማኖትን የሚጠብቁና ክርስቶስን የሚስል አሸናፊ ሕይወት የሚታይባቸው ወይም ኢግብረገባዊነትና እምነተ ቢስነት የከበረውን ሁሉ ያወድምባቸው እንደሆን አካሄዳቸው ይወስናል፡፡Gospel Workers p. 68. ChSAmh 42.1