የክርስቲያን አገልግሎት

15/246

በወጣትነቱ ለአገልግሎት የተመረጠው ጢሞቴዎስ

የጢሞቴዎስን ታማኝነት፣ ጽኑና እውነተኝነት የተመለከተው ጳውሎስ የሥራው አጋር ሆኖ አብሮት ለአገልግሎት እንዲጓዝ መረጠው:: ጢሞቴዎስን ከለጋ ዕድሜው አንስቶ ኮትኩተው ያሳደጉ ወገኖች በእነርሱ ጥንቃቄ ውስጥ ያለፈው ወጣት ከታላቁ ሐዋርያ ጋር የቀረበ ግንኙነት መስርቶ መመልከታቸው የከበረ ስሜት ፈጠረባቸው፡፡ ጢሞቴዎስ የመምህርነት አገልግሎት እንዲሰጥ በእግዚአብሔር ሲመረጥ ገና ወጣት ቢሆንም፤ በለጋ ዕድሜው የቀሰማቸው መርኅዎች ለጳውሎስ ረዳት የሚያደርገውን ኃላፊነት በብቃት እንዲይዝ አድርገውት ነበር፡፡ ምንም እንኳ ጢሞቴዎስ ገና ወጣት ቢሆንም እንደ አንድ ቅን ክርስቲያን የተጣለበትን ኃላፊነትና አደራ ይወጣ ነበር፡፡ The Acts of the Apostles, pp. 203, 204. ChSAmh 41.3